ዘዳግም 5:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ያ ብርቱ እሳት ያጠፋናል፤ ታዲያ ለምን መሞት እንፈልጋለን? እግዚአብሔር አምላካችን እንደገና ቢናገረን እንሞታለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእንግዲህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ ብንሰማ እንሞታለን፤ ይህችም ታላቅ እሳት ፈጽማ ታጠፋናለች፤ ታዲያ ለምን እንሙት? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና፥ እንግዲያውስ አሁን ለምን እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን የጌታን ድምፅ ደግመን ከሰማን እንሞታለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አንሙት፤ ይህችም ታላቅ እሳት አታጥፋን፤ እኛ የአምላካችን የእግዚአብሔርን ድምፅ ዳግመኛ ብንሰማ እንሞታለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን እንግዲህ ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን። |
ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤
“በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ትእዛዞች ሁሉ ጸንቶ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ “ሕግን በመፈጸም እንጸድቃለን” የሚሉ ሁሉ የተረገሙ ናቸው።
“በሲና ተራራ ላይ በተሰበሰባችሁበት ቀን እሞታለሁ ብለህ በመፍራት እግዚአብሔር ዳግመኛ እንዳይናገርህና የመገለጡን ሁኔታ የሚያመለክተውን አስፈሪ እሳት እንዳታይ ጠይቀህ ነበር።
ሙሴም እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጣ፤ ከኤዶም ላይ እንደ ንጋት ፀሐይ አበራ፤ ከፋራንም ተራራ ላይ አንጸባረቀ፤ በስተቀኙ የእሳት ነበልባል ነበር፤ ከእርሱም ጋር አእላፍ መላእክት ነበሩ።
እንዲህ አላችሁ፦ ‘በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር በሰማነው ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን ታላቅነቱንና ክብሩን በግልጥ አሳይቶናል፤ እግዚአብሔር ካነጋገረው በኋላ እንኳ ሰው በሕይወት መኖር እንደሚችል በዛሬው ዕለት አይተናል።
የእምቢልታ ድምፅ ወይም የሚነገረው ቃል ወደሚሰማበትም አልደረሳችሁም፤ ያንን ቃል የሰሙ ሰዎች “ከእንግዲህ ወዲህ ሌላ ቃል አይነገረን” በማለት እስከ መለመን ደርሰዋል።