ወደ ሲና ተራራ ወርደህ ከሰማይ ሕዝብህን አነጋገርካቸው፤ ትክክለኛና ፍትሓዊ ሕግንና ሥርዓትን፥ መልካም የሆኑትን ደንቦችንና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው።
ዘዳግም 4:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቱንስ ያኽል ታላቅ ቢሆን ዛሬ እኔ በፊታችሁ ቆሜ እንደማስተምራችሁ እንደዚህ ያለ ትክክልና ቅን የሆነ ሕግና ሥርዓት ያለው ሕዝብ የት ይገኛል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ እኔ በፊታችሁ እንዳስቀመጥሁት ሕግ ያለ ጽድቅ የሆነ ሥርዐትና ሕግ ያሉት ሌላ ታላቅ ሕዝብስ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓይናችሁ ፊት ዛሬ እንዳኖርኩት እንደዚህ ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆነች ሥርዓትና ሕግጋት ያለው ታላቅ ሕዝብስ የት ይገኛል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬ በፊታችሁ እንደማኖራት እንደዚህች ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆነች ሥርዐትና ፍርድ ያለው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓይናችሁ ፊት ዛሬ እንደማኖራት እንደዚህች ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆነች ሥርዓትና ፍርድ ያለው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው? |
ወደ ሲና ተራራ ወርደህ ከሰማይ ሕዝብህን አነጋገርካቸው፤ ትክክለኛና ፍትሓዊ ሕግንና ሥርዓትን፥ መልካም የሆኑትን ደንቦችንና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው።
ይህን ብታደርግ ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ በምስጋና፥ በስም፥ በክብርም ከፍ ሊያደርግህና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ እንደሚያደርግህ ነግሮሃል።”