ዘዳግም 33:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ነገዶችና የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ነገሠ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋራ ሆነው፣ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፣ እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፥ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፥ እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ጋር በተሰበሰቡ ጊዜ፥ አለቃ በተወዳጁ ዘንድ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች 2 ሁሉ ጋር በተከማቹ ጊዜ፥ 2 ንጉሥ በይሹሩን ነበረ። |
በእስራኤል ሕዝብ ላይ ክፉ አጋጣሚ ወይም ችግር እንደማይደርስባቸው ይታያል፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ነው፤ እግዚአብሔር ንጉሥ መሆኑንም በይፋ ይናገራሉ።
ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ጌዴዎንን “አንተ ከምድያማውያን እጅ አድነኸናልና አንተና ከአንተም በኋላ ልጆችህ እንዲሁም የልጅ ልጆችህ ገዢዎቻችን ሁኑ፤” አሉት።
“ለሴኬም ሰዎች ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ንገሩአቸው፦ ‘የጌዴዎን ሰባ ልጆች፥ ወይስ አንድ ሰው ብቻ ቢገዛችሁ ይሻላል? እኔ ደግሞ ለእናንተ የአጥንታችሁ ፍላጭ የሥጋችሁ ቊራጭ መሆኔን አስታውሱ።’ ”