“እንግዲህ ሂዱና እኔና የይሁዳ ነዋሪ ሕዝብ በዚህ በተገኘው መጽሐፍ ስላለው ትምህርት ማወቅ እንችል ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን መመሪያ ስላልተከተሉ እግዚአብሔር በእኛ ላይ በጣም ተቈጥቶአል።”
ዘዳግም 31:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባዕዳን አማልክትን በማምለክ በሠሩት ኃጢአት እኔ በዚያ ጊዜ ፈጽሞ አልረዳቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ባዕዳን አማልክት በመዞር ከፈጸሙት ክፋታቸው የተነሣ፣ በዚያች ቀን ፊቴን ከእነርሱ ፈጽሞ እሰውራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ባዕዳን አማልክት በመዞር ከፈጸሙት ክፋታቸው የተነሣ፥ በዚያች ቀን ፊቴን ከእነርሱ ፈጽሞ እሰውራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌሎችን አማልክት ተከትለዋልና ስላደረጉት ክፋት ሁሉ እኔ በዚያ ቀን ፈጽሜ ፊቴን እሰውራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎችን አማልክት ተከትለዋልና ስላደረጉት ክፋት ሁሉ እኔ በዚያ ቀን ፈጽሜ ፊቴን እሰውራለሁ። |
“እንግዲህ ሂዱና እኔና የይሁዳ ነዋሪ ሕዝብ በዚህ በተገኘው መጽሐፍ ስላለው ትምህርት ማወቅ እንችል ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን መመሪያ ስላልተከተሉ እግዚአብሔር በእኛ ላይ በጣም ተቈጥቶአል።”
ለከንቱ አማልክታቸው ሲሰግዱና መሥዋዕት ሲሠዉላቸው እንድትተባበሩአቸው ስለሚጠይቁአችሁ፥ እናንተም እነርሱ ለአማልክታቸው የሚያቀርቡትን ምግብ ለመብላት ስለምትፈተኑ፤ በአገሩ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ።
እኔ የምናገረውን አትሰሙም፤ ለማወቅም አትፈልጉም፤ ከጥንት ጀምሮ ጆሮአችሁ የተደፈነ ነው፤ ይህም የሆነው እናንተ በጣም ከዳተኞች መሆናችሁንና ከተወለዳችሁ ጀምሮ ዐመፀኞች ተብላችሁ መጠራታችሁን ዐውቃለሁ።
እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ በጣም ተቈጥቶአል፤ በኀያልነቱም ይቀጣቸዋል፤ ተራራዎች ይናወጣሉ፤ የሞቱ ሰዎችም አስከሬን እንደ ጥራጊ በየመንገዱ ዳር ይወድቃል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ አይበርድም፤ እንደገናም ሊቀጣቸው ተዘጋጅቶአል።
በኃጢአታችን ምክንያት ፊትህን ስላዞርክብንና ለበደላችንም ተገዢዎች እንድንሆን ስለ ተውከን ስምህን የሚጠራና አንተን ለማግኘት የሚጥር ማንም የለም።
ከሕዝቡ መካከል ከባቢሎናውያን ጋር በሚዋጉበት ጊዜ ከክፋታቸው የተነሣ እኔ ፊቴን ከዚህች ከተማ ስላዞርኩ በቊጣዬና በመዓቴ በምገድላቸው ሬሳዎች ቤቶቹ የተሞሉ ይሆናሉ።
እስራኤላውያን ተማርከው የሄዱትም እኔን በመበደላቸው ምክንያት መሆኑን ሕዝቦች ሁሉ ያውቃሉ፤ እኔ ችላ ስላልኳቸው ጠላቶቻቸው በጦርነት ድል አድርገው ሁላቸውንም ገድለዋቸዋል።
ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ለመሪዎቻቸው የማይታዘዙ ሆኑ፤ ለእግዚአብሔርም ያላቸውን ታማኝነት አጓድለው የሌሎች ባዕዳን አማልክት አገልጋዮች ሆኑ፤ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ያከብሩ ነበር፤ እነርሱ ግን የአባቶቻቸውን ምሳሌ አልተከተሉም።