Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 22:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “እንግዲህ ሂዱና እኔና የይሁዳ ነዋሪ ሕዝብ በዚህ በተገኘው መጽሐፍ ስላለው ትምህርት ማወቅ እንችል ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን መመሪያ ስላልተከተሉ እግዚአብሔር በእኛ ላይ በጣም ተቈጥቶአል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ሂዱና ስለ እኔ፣ ስለ ሕዝቡና ስለ ይሁዳም ሁሉ በተገኘው በዚህ መጽሐፍ ስለ ተጻፈው ነገር እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ምክንያቱም አባቶቻችን ለዚህ መጽሐፍ ቃል ባለመታዘዛቸው፣ እኛን በተመለከተም በዚሁ ላይ የተጻፈውን ሁሉ ባለመፈጸማቸው፣ በእኛ ላይ የነደደው የእግዚአብሔር ቍጣ ታላቅ ነውና።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “እንግዲህ ሂዱና እኔና የይሁዳ ነዋሪ ሕዝብ በዚህ በተገኘው መጽሐፍ ስላለው ትምህርት ማወቅ እንችል ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን መመሪያ ስላልተከተሉ እግዚአብሔር በእኛ ላይ በጣም ተቆጥቶአል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “አባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ር​ስዋ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚ​ህ​ችን መጽ​ሐፍ ቃል ስላ​ል​ሰሙ በላ​ያ​ችን የነ​ደደ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳ​ችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁ​ዳም ሁሉ ስለ​ዚ​ችም ስለ​ተ​ገ​ኘ​ችው መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 “አባቶቻችን በእርስዋ የተጻፈውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚህችን መጽሐፍ ቃል ስላልሰሙ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁዳም ሁሉ የዚህችን የተገኘችውን መጽሐፍ ቃል እግዚአብሔርን ጠይቁ፤” ብሎ አዘዛቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 22:13
37 Referencias Cruzadas  

ታላቁ የቊጣ ቀን መጥቶአል፤ ማን ሊቋቋመው ይችላል?” አሉአቸው።


ቀድሞ ሕግ ባልነበረበት ጊዜ እኔ በሕይወት እኖር ነበር፤ የሕግ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን እኔ ሞቼ ኃጢአት ሕይወት አገኘ።


ሕግ የሚያመጣው የእግዚአብሔርን ቊጣ ነው፤ ሕግ ከሌለ ግን ሕግን የመተላለፍ በደል አይኖርም።


ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም፤ ሕግ የሚያሳየው ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው።


በእርሱ ኀይለኛ ቊጣ ፊት መቆም የሚችል ማን ነው? ቊጣውስ እንደ እሳት በነደደ ጊዜ የሚችለው ማነው? እንደ እሳት የሚያቃጥል ቊጣው በሚወርድበት ጊዜ አለቶች ተሰነጣጥቀው ይበታተናሉ።


ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት አስቀድሞ ሳይገልጥ ምንም ነገር አያደርግም።


እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ሕጎችህን በመጠበቅ ታዛዦች ሆነን አልተገኘንም፤ በአገልጋዮችህ በነቢያት አማካይነት የሰጠኸንን ትእዛዞች አልጠበቅንም።


አባቶቻችን ኃጢአት ሠርተው አለፉ፤ እኛ ግን የእነርሱን ኃጢአት እንሸከማለን።


እኛ እንፈጽማለን ብለን ያሰብነውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ የሰማይ ንግሥት ተብላ ለምትጠራው አምላካችን ዕጣን እናጥናለን፤ እኛና የቀድሞ አባቶቻችን፥ ንጉሦቻችንና መሪዎቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ስናደርግ በነበረው ዐይነት አሁንም የወይን ጠጅ መባ እናቀርብላታለን። ይህን ሁሉ በምናደርግበት በዚያን ጊዜ ብዙ ሲሳይ ነበረን፤ ባለጸጎችም ስለ ነበርን ምንም ችግር አልነበረብንም።


ዘግየት ብሎም ንጉሥ ሴዴቅያስ መልእክተኛ ልኮ አስወሰደኝና በቤተ መንግሥቱ በግል ሲያነጋግረኝ “ከእግዚአብሔር የተነገረህ የትንቢት ቃል አለን?” ብሎ ጠየቀኝ። “አዎ፥ አለ!” ብዬ ንግግሬን በመቀጠል “አንተ ለባቢሎን ንጉሥ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አልኩት።


እናንተ ደግሞ ከቀድሞ አባቶቻችሁ የባሰ ክፉ ነገር አደረጋችሁ፤ ሁላችሁም እልኸኞችና ዐመፀኞች ሆናችሁ፤ ለእኔም አትታዘዙም።


በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔርን መሪ አድርገው፤ እርሱም በትክክለኛው መንገድ ይመራሃል።


እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ኃጢአት ሠርተናል፤ ተሳስተናል፤ በደለኞችም ሆነናል።


እግዚአብሔር ሆይ አንተ ግን በሁሉ ዘንድ የተፈራህ ነህ፤ አንተ ስትቈጣ በፊትህ የሚቆም አንድ እንኳ አይኖርም፤


እግዚአብሔር ለሚታዘዙት ሁሉ ወዳጃቸው ነው፤ ለእነርሱ የገባውንም ቃል ኪዳን ያጸናል።


እዚያው እንደ ቆሙም፥ የአምላካቸው የእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ሦስት ሰዓት ሙሉ ተነበበላቸው፤ ሌላም ሦስት ሰዓት ኃጢአታቸውን በመናዘዝ፥ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።


“ሄዳችሁ ስለ እኔና እንዲሁም በእስራኤልና በይሁዳ ስለ ቀረው ሕዝብ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ በዚህ መጽሐፍ ስላለውም ትምህርት አረጋግጡ፤ የቀድሞ አባቶቻችን ለእግዚአብሔር ቃል ባለመታዘዛቸውና ይህ መጽሐፍ አድርጉ የሚላቸውን ሁሉ ባለመፈጸማቸው፥ እግዚአብሔር ቊጣውን በእኛ ላይ አውርዶአል።”


የቀድሞ አባቶቻችን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት አጓድለዋል፤ እርሱንም በመተው የእርሱ መኖሪያ ከሆነው ስፍራ ፊታቸውን አዞሩ፤


ንጉሥ ኢዮሣፍጥም “በእርሱ አማካይነት እግዚአብሔርን መጠየቅ እንድንችል በዚህ አንድም ነቢይ የለምን?” ሲል ጠየቀ። ከንጉሥ ኢዮራም ሠራዊት አዛዦች አንዱ፥ “ቀድሞ የኤልያስ ረዳት የነበረው የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ እዚህ አለ” ሲል መልስ ሰጠ።


እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።


እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ በጣም ተቈጥቶአል፤ በኀያልነቱም ይቀጣቸዋል፤ ተራራዎች ይናወጣሉ፤ የሞቱ ሰዎችም አስከሬን እንደ ጥራጊ በየመንገዱ ዳር ይወድቃል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ አይበርድም፤ እንደገናም ሊቀጣቸው ተዘጋጅቶአል።


እግዚአብሔር አስፈሪ በሆነው ቊጣና መዓቱ ሕዝቡን እንደሚቀጣ የተናገረ በመሆኑ ምናልባት በመጸጸት ከክፉ ሥራቸው ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ይለምኑት ይሆናል።”


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ነገር ግን እኔን ባትሰሙና እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ባትፈጽሙ፥


“ ‘እነዚህን የእግዚአብሔርን ሕግ ቃላት ሁሉ የማይፈጽም ሁሉ የተረገመ ይሁን።’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን’ ይበሉ።


ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቊጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።


ፍርድህን ከሰማይ እንዲታወቅ ስታደርግ ምድሪቱ ፈርታ ጸጥ አለች፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios