ዘዳግም 3:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህም የተነሣ በቤትፔዖር ከተማ ፊት ለፊት ባለው ሸለቆ ውስጥ ቈየን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እኛ በቤተ ፌጎር አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ቈየን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እኛም በቤተፌዖር ፊት ለፊት በሸለቆው ውስጥ ተቀመጥን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤተ ፌጎርም ፊት ለፊት በሸለቆው ውስጥ ተቀመጥን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤተፌጎርም ፊት ለፊት በሸለቆው ውስጥ ተቀመጥን። |
እግዚአብሔርም ከቤትፐዖር ከተማ ፊት ለፊት በሞአብ አገር በሚገኘው ሸለቆ ቀበረው፤ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እርሱ የተቀበረበትን ትክክለኛ ቦታ ለይቶ የሚያውቅ የለም።
በፔዖር ተራራ ላይ እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ራሳችሁ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ይኸውም በዚያ ተራራ ላይ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት የሚሰግዱትን ሁሉ ደምስሶአል፤
እነዚህንም ያወጀው በዮርዳኖስ ማዶ በቤትፔዖር ሸለቆ ፊት ለፊት የአሞራውያን ንጉሥ በነበረው በሐሴቦን በነገሠውና ሙሴና እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ተዋግተው ባሸነፉት በሲሖን ምድር ነው።