ንጉሥ ኢዮአካዝ ከኀምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥር ሠረገሎችና ከዐሥር ሺህ ወታደሮች በቀር ሌላ የተደራጀ የጦር ኀይል አልነበረውም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሌላውን ሠራዊቱን የሶርያ ንጉሥ በአውድማ እንዳለ እብቅ ስለ ደመሰሰበት ነው።
ዘዳግም 28:62 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሆናችሁ ስላልተገኛችሁ ብዛታችሁ እንደ ሰማይ ከዋክብት ከነበራችሁት ከእናንተ ጥቂቶቹ ብቻ ይተርፋሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስላልታዘዛችሁ፣ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝታችሁ የነበራችሁት እናንተ ጥቂት ብቻ ትቀራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ ለእግዚአብሔር ስላልታዘዛችሁ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝታችሁ የነበራችሁት እናንተ ጥቂት ብቻ ትቀራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁምና ከብዛታችሁ የተነሣ እንደ ሰማይ ከዋክብት የነበረው ቍጥራችሁ ጥቂት ሆኖ ይቀራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁምና ከብዛታችሁ የተነሣ እንደ ሰማይ ከዋክብት የነበረው ቁጥራችሁ ጥቂት ሆኖ ይቀራል። |
ንጉሥ ኢዮአካዝ ከኀምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥር ሠረገሎችና ከዐሥር ሺህ ወታደሮች በቀር ሌላ የተደራጀ የጦር ኀይል አልነበረውም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሌላውን ሠራዊቱን የሶርያ ንጉሥ በአውድማ እንዳለ እብቅ ስለ ደመሰሰበት ነው።
ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።
ብዛታቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የሆኑ ልጆችን ሰጠሃቸው፥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ትሰጣቸው ዘንድ ቃል የገባህላቸውን ምድር፥ በድል አድራጊነት እንዲይዙ ፈቀድክላቸው።
ስለዚህም ርግማን ምድርን ያጠፋል፤ ሕዝቦችዋም በበደሉት በደል ተጠያቂዎች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይደመሰሳሉ፤ የሚተርፉትም ጥቂቶች ናቸው።
እኔም “አቤቱ ጌታ ሆይ፥ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” ብዬ ጠየቅሁ። እርሱም “ከተሞች እስኪፈርሱ፥ ቤቶችም የሚኖርባቸው አጥተው ወና እስኪሆኑና አገሪቱም የተፈታች ባድማ እስክትሆን ድረስ ነው።
ከዐሥሩ አንድ ክፍል ቢተርፍም እንኳ እርሱም እንደ ግራር ወይም እንደ ዋርካ እንደገና ይቃጠላል። ዛፉ ሲቈረጥ ጉቶው ይቀራል። ጉቶውም የተቀደሰ ዘር ነው።”
“እባክህ የምንጠይቅህን ነገር አድርግልን! ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን! ከስደት ለተረፍነው ሁሉ ጸልይልን! ቀድሞ ብዙዎች ነበርን፤ አሁን ግን አንተ ራስህ እንደምታየን ጥቂቶች ብቻ ቀርተናል፤
በመካከላችሁ አደገኞች አራዊትን እልካለሁ፤ እነርሱም ልጆቻችሁን ይገድላሉ፤ ከብቶቻችሁንም ያወድማሉ፤ ከእናንተ ጥቂት ሰዎች ብቻ ስለሚቀሩ ጐዳናዎቻችሁ ሁሉ ሰው አልባ ይሆናሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከአንዲት የእስራኤል ከተማ ሺህ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ በሕይወት የሚቀሩት ግን አንድ መቶ ብቻ ይሆናሉ፤ ከሌላይቱም ከተማ መቶ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ ተመልሰው የሚመጡት ግን ዐሥር ብቻ ይሆናሉ።”
የቀድሞ አባቶችህ ወደ ግብጽ በወረዱ ጊዜ ብዛታቸው ሰባ ብቻ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር አምላክህ የአንተን ቊጥር ብዛት እንደ ሰማይ ከዋክብት አድርጎታል።