Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 26:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በመካከላችሁ አደገኞች አራዊትን እልካለሁ፤ እነርሱም ልጆቻችሁን ይገድላሉ፤ ከብቶቻችሁንም ያወድማሉ፤ ከእናንተ ጥቂት ሰዎች ብቻ ስለሚቀሩ ጐዳናዎቻችሁ ሁሉ ሰው አልባ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የዱር አራዊትን እሰድድባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁን ይነጥቋችኋል፤ ከብቶቻችሁን ያጠፉባችኋል፤ ቍጥራችሁ ይመነምናል፤ መንገዶቻችሁም ሰው አልባ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በመካከላችሁም የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይነጥቁአችኋል፥ እንሰሶቻችሁንም ያጠፉባችኋል፥ እናንተንም ቁጥራችሁን ያመነምኑታል፤ መንገዶቻችሁም የተራቈቱ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በእ​ና​ንተ ላይ ክፉ​ዎች የም​ድ​ርን አራ​ዊት እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ይበ​ሉ​አ​ች​ኋል፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ያጠ​ፋሉ፤ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ን​ሳሉ፤ መን​ገ​ዶ​ቻ​ች​ሁም በረሃ ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በመካከላችሁም የምድርን አራዊት እሰድዳለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይነጥቃሉ፥ እንሰሶቻችሁንም ያጠፋሉ፥ እናንተንም ያሳንሳሉ፤ መንገዶቻችሁም በረሃ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 26:22
17 Referencias Cruzadas  

“በዚያች አገር አውሬ ሰድጄ ሰው አልባ እስከሚሆንና ማንም በዚያ በኩል ማለፍ እስከማይችል ድረስ አገሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ።


የሚጨርስ ራብ በእነርሱ ላይ እልካለሁ፤ በወረርሽኝና በመቅሠፍት ያልቃሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችንና መርዘኛ ተናዳፊ እባቦችን እሰድባቸዋለሁ።


በዐናት ልጅ በሻምጋርና በያዔል ዘመን፥ የሲራራ ነጋዴዎች በምድሪቱ አያልፉም ነበር፤ መንገደኞችም ተደብቀው በዘወርዋራ መንገድ ይሄዱ ነበር፤


እንደ ዐውሎ ነፋስ ጠራርጌ በመውሰድም በማያውቁት ባዕድ አገር እንዲኖሩ አደረግኋቸው፤ ይህችም መልካም ምድር ማንም የማይኖርባት ባድማ ሆና ቀረች፥ ያቺ ያማረች ምድርም ባድማ ሆነች።”


ማንም ሰው በዓላቱን ለማክበር ስለማይመጣ የጽዮን መንገዶች ጭር ይላሉ፤ በሮችዋ ሁሉ ባዶ ናቸው፤ ካህናትዋ ይቃትታሉ ልጃገረዶችዋ በሐዘን ይጨነቃሉ የጽዮንም ዕድል ፈንታ የመረረ ይሆናል።


አውራ ጐዳናዎች ባዶ ሆኑ፤ በመንገዶቹ ላይ ተጓዦች የሉም፤ ቃል ኪዳን ፈረሰ፤ የውል ስምምነቶች ተጥሰዋል፤ ከዚህም የተነሣ ምክር የሚሰጠው ሰው አልተገኘም።


እነርሱም በዚያ ሰፍረው መኖር እንደ ጀመሩ እግዚአብሔርን አላመለኩትም ነበር። ስለዚህም እግዚአብሔር አንበሶችን በመላክ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ሰባብረው እንዲገድሉ አደረገ፤


“በምድራችሁ ሰላምን እሰጣችኋለሁ፤ ማንንም ሳትፈሩ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ አደገኞች የሆኑ አራዊትን ከምድራችሁ አስወግዳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ጦርነት በዚያ አይኖርም።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ይሆናል።


ምድሪቱንም ባድማና ወና አደርጋታለሁ፤ ዕብሪተኛ ኀይልዋም ያበቃል፤ የእስራኤል ተራራዎች ማንም በዚያ በኩል የማያልፍባቸው ባዶ ይሆናሉ።


ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ሕዝብንና እንስሶችን በአንድነት ለመጨረስ ጦርነትን፥ ራብን፥ አራዊትንና ቸነፈርን እነዚህን እጅግ የከፉ አራት መቅሠፍቶች በኢየሩሳሌም ላይ አመጣለሁ።


ራብንና የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይገድላሉ፤ ጦርነትንም አመጣባችኋለሁ፤ መቅሠፍትና ግድያም በመካከላችሁ ይስፋፋል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እኔ እግዚአብሔር አራት ክፉ ነገሮች እንዲደርሱባቸው ወስኛለሁ፤ ስለዚህ በጦርነት ይሞታሉ፤ ሬሳቸውን ውሾች ይጐትቱታል፤ ወፎች ሥጋቸውን ይበሉታል፤ የተረፈውን አራዊት ይግጡታል፤


ስለዚህም ርግማን ምድርን ያጠፋል፤ ሕዝቦችዋም በበደሉት በደል ተጠያቂዎች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይደመሰሳሉ፤ የሚተርፉትም ጥቂቶች ናቸው።


በዚያን ጊዜ በየስፍራው ሁሉ ሁከትና ሽብር ስለ ነበር፥ በሰላም ወጥቶ የሚገባ ማንም አልነበረም፤


ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው።


“እባክህ የምንጠይቅህን ነገር አድርግልን! ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን! ከስደት ለተረፍነው ሁሉ ጸልይልን! ቀድሞ ብዙዎች ነበርን፤ አሁን ግን አንተ ራስህ እንደምታየን ጥቂቶች ብቻ ቀርተናል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios