“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፥ እንዲሁም በውርጭ በዋግና በአንበጣ ወይ በኩብኩባ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ፥ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ፥ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፥
ዘዳግም 28:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛፎችህንና የእርሻ ሰብልህን ሁሉ ኲብኲባ ይበላዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛፍህንና የምድርህን ሰብል ሁሉ የአንበጣ መንጋ ይወርረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛፍህንና የምድርህን ሰብል ሁሉ ኩብኩባ ይወረዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛፍህን ሁሉ፤ የምድርህንም ፍሬ ሁሉ ኩብኩባ ያጠፋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛፍህን ሁሉ የምድርህንም ፍሬ ኩብኩባ ይወርሰዋል። |
“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፥ እንዲሁም በውርጭ በዋግና በአንበጣ ወይ በኩብኩባ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ፥ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ፥ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፥
“ሰብላችሁን የሚያደርቅ ብርቱ ነፋስ ላክሁባችሁ፤ አትክልታችሁንና የወይን ተክላችሁን የበለስና የወይራ ዛፋችሁን ሁሉ አንበጣ በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።