ዘዳግም 27:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነዚያም ድንጋዮች ላይ የእግዚአብሔርን ሕግጋት ሁሉ በግልጥ እንዲነበቡ አድርገህ ጻፍ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድንጋዮቹ ላይ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርገህ ጻፍባቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ ግልጽ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተገለጠ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተገለጠ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ። |
“እስከ አሁን በምሳሌ ነገርኳችሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ በምሳሌ የማልናገርበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ስለ አብ ሁሉን ነገር ገልጬ እነግራችኋለሁ።
ሙሴም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ሆኖ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ከልብ ሆነህ አድምጠኝ፤ እነሆ፥ ዛሬ የአምላክህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነሃል፤
የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እስራኤላውያንን ባዘዘው መሠረት በሙሴ አማካይነት በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ ውስጥ እንደ ተጻፈው ባልተጠረበና ብረት ባልነካው ድንጋይ መሠዊያ ሠርተው የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድነት ቊርባን አቀረቡ።