ኢያሱ 8:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እስራኤላውያንን ባዘዘው መሠረት በሙሴ አማካይነት በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ ውስጥ እንደ ተጻፈው ባልተጠረበና ብረት ባልነካው ድንጋይ መሠዊያ ሠርተው የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድነት ቊርባን አቀረቡ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 መሠዊያውንም የሠራው የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ፣ እስራኤላውያንን ባዘዛቸው መሠረት ሲሆን፣ ይህንም የሠራው በሙሴ የሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው ባልተጠረበና የብረት መሣሪያ ባልነካው ድንጋይ ነው፤ በዚህም ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ የኅብረት መሥዋዕትም ሠዉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 የጌታ ባርያ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዘ፥ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደተጻፈው፥ “መሠዊያው ካልተወቀረና ብረት ካልነካው ድንጋይ ነበረ”፤ በእርሱም ላይ ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የአንድነትንም መሥዋዕት ሠዉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዘ፥ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፥ መሠዊያው ካልተወቀረና ብረት ካልነካው ድንጋይ ነበረ፤ በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ፤ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዋ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዘ፥ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፥ መሠዊያው ካልተወቀረና ብረት ካልነካው ድንጋይ ነበረ፥ በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዉ። Ver Capítulo |