ካህን የሆነ ሁሉ ባልዋ የሞተባትን ወይም ከባልዋ የተፋታችውን ሴት ማግባት አይፈቀድለትም፤ ነገር ግን ድንግል የሆነችውን እስራኤላዊት ልጃገረድ ወይም ካህን የሆነ ባልዋ የሞተባትን ሴት ማግባት ይችላል።
ዘዳግም 24:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም ሌላ ባል ታገባ ይሆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቤቱ ከወጣች በኋላ ሌላ ባል ብታገባ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቤቱ ከወጣች በኋላ ሌላ ባል ብታገባ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቤቱም ከወጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቤቱም ከወጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ |
ካህን የሆነ ሁሉ ባልዋ የሞተባትን ወይም ከባልዋ የተፋታችውን ሴት ማግባት አይፈቀድለትም፤ ነገር ግን ድንግል የሆነችውን እስራኤላዊት ልጃገረድ ወይም ካህን የሆነ ባልዋ የሞተባትን ሴት ማግባት ይችላል።
ባልዋ የሞተባትን ወይም አግብታ የተፋታችውን ወይም ክብረ ንጽሕናዋ የተደፈረውን፥ ወይም አመንዝራ የነበረችውን ሴት አያግባ፤ ድንግል የሆነችውን ብቻ ወገኑ ከሆኑ ሕዝብ መካከል መርጦ ያግባ።
ካህናት ለአምላካቸው ተለይተው የተቀደሱ ስለ ሆኑ፥ አመንዝራ የነበረች ሴት፥ ወይም ክብረ ንጽሕናዋ የተደፈረ ልጃገረድ ወይም አግብታ የፈታች ሴት አያግቡ፤
ነገር ግን ልጅ ሳትወልድ ባልዋ የሞተባት ወይም ከባልዋ በመፋታት ወደ አባቷ ቤት ተመልሳ መጥታ በጥገኝነት የምትኖር የካህኑ ልጅ በልጅነትዋ ታደርገው እንደ ነበረው ሁሉ የአባቷ ድርሻ ከሆነው ቅዱስ ነገር ትብላ፤ ሆኖም ከካህኑ ቤተሰብ ሌላ ሰው የተቀደሰውን ነገር መብላት የለበትም።
ባልዋ የሞተባት ሴት ወይም ከባልዋ የተፋታች ሴት ማንኛቸውንም ስእለት ሆነ ወይም ከአንድ ነገር ለመከልከል የገባችውን ቃል መፈጸም አለባት።
እኔ ግን “በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር፥ ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ እንድታመነዝር ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ አመንዝራ ይሆናል” እላችኋለሁ።
ክርስቲያን ያልሆነ ወገን መለየት ከፈለገ ይለይ፤ በዚህ ጊዜ ግን ክርስቲያን የሆነው ወገን ባልም ሆነ ሚስት በምንም ዐይነት ግዴታ አይያዝም። እግዚአብሔር የጠራን በሰላም እንድንኖር ነው።
“አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ እርስዋን የማይወድበትን ነገር በማግኘቱ ቢጠላት የፍች የምስክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ያባርራታል፤
ሁለተኛውም ባል ስለሚጠላት የተፈታችበትን ምክንያት የሚገልጥ የፍች ደብዳቤ ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ያባርራታል፤ ወይም ሁለተኛው ባልዋ ይሞት ይሆናል፤