ዘዳግም 22:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጫጩቶቹን መውሰድ ትችላለህ፤ እናቲቱን ወፍ ግን እንድትበር ልቀቃት፤ ይህን ብታደርግ ሀብታም ሆነህ ለረጅም ዘመን ትኖራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጫጩቶቿን መውሰድ ትችላለህ፤ እናቲቱን ግን መልካም እንዲሆንልህና ዕድሜህም እንዲረዝም ልቀቃት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም እንዲረዝም፥ ጫጩቶቹን መውሰድ ትችላለህ፤ እናቲቱን ግን ልቀቃት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን መልካም ይሆንልህ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ እናቲቱን ልቀቅ፤ ጫጭቶችንም ለአንተ ውሰድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን መልካም ይሆንልህ ዘንድ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ እናቲቱን ስደድ፥ ጫጩቶችንም ለአንተ ውሰድ። |
እግዚአብሔር አምላካችሁ ለዘለዓለም እንድትኖሩባት በሚያወርሳችሁ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ ለእናንተና ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላቸው እኔ ዛሬ የማዛችሁን ሕጉንና ትእዛዞቹን ጠብቁ።”