ዘዳግም 22:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤላዊ ወገንህ ንብረት የሆነ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታገኝ ዝም ብለህ አትለፈው፤ ወደ ባለቤቱ መልሰህ ውሰድለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታየው፣ ወደ እርሱ መልሰህ አምጣለት እንጂ ዝም ብለህ አትለፈው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፥ ወደ ወንድምህ መልሰው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የወንድምህ በሬ ወይም በግ በመንገድ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፤ እነርሱን መልሰህ ለወንድምህ ስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፤ ወደ ወንድምህ መልሰው። |
ወዳጆችህን ወይም የአባትህን ወዳጆች አትርሳ፤ ችግር ሲደርስብህ የወንድምህን ርዳታ አትጠይቅ፤ ከሩቅ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጐረቤት ይጠቅምሃል።
ምግባችሁን ከተራበ ሰው ጋር እንድትካፈሉ፥ ማደሪያ የሌለውን ድኻ በቤታችሁ እንድትቀበሉ፥ የተራቈቱትን እንድታለብሱ፥ ከቅርብ ዘመዶቻችሁም ራሳችሁን እንዳትደብቁ አይደለምን?
“የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትን እመልሳለሁ፤ የተሰበሩትን እጠግናለሁ፤ ደካሞችን አበረታለሁ፤ እኔ ትክክለኛ እረኛ ስለ ሆንኩ በግፍ የሰቡትንና ብርቱዎች የሆኑትን አጠፋለሁ።
የደከሙትን አላበረታቸሁም፤ የታመሙትን አላዳናችሁም፤ የተሰበሩትን አልጠገናችሁም፤ የባዘኑትን አልመለሳችሁም፤ የጠፉትን አልፈለጋችሁም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በግፍና በጭካኔ ገዛችኋቸው።
“እኔ የሠራዊት አምላክ ለሕዝቤ የሰጠሁት ትእዛዝ ይህ ነበር፤ ‘በትክክል ፍረዱ፥ እርስ በርሳችሁም አንዳችሁ ለሌላው ምሕረትና ርኅራኄን አድርጉ፤
ነገር ግን ባለቤቱ የሚኖርበት ቦታ ሩቅ ቢሆን፥ ወይም ባለቤቱ ማን እንደ ሆነ ካላወቅህ እንስሳውን ወደ ቤትህ ውሰደው፤ እርሱን ሊፈልግ በሚመጣበት ጊዜ ለባለቤቱ ስጠው፤