ዘዳግም 21:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ሁለት ሚስቶችን አግብቶ አንደኛይቱን አፍቅሮ ሌላይቱን ባያፈቅርና ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ቢወልዱለት፥ ምናልባት የመጀመሪያው ልጅ የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፣ አንደኛዋን የሚወድዳት፣ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፣ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት በኵር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወድዳት ሚስቱ ቢሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፤ አንደኛዋን የሚወዳት፥ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፥ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት በኩር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች፥ አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው፥ ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኩሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥ |
ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለ ነበር የቈየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።
እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር እንዳልተወደድኩ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ስምዖን አለችው።
ታዲያ፥ ያ ሰው ሀብቱንና ንብረቱን ለልጆቹ በሚያካፍልበት ጊዜ ለበኲር ልጁ ሊሰጥ የሚገባውን ድርሻ በተለይ ከሚያፈቅራት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በመስጠት አድልዎ ማድረግ አይገባውም፤