ዘዳግም 20:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በአንዲት ከተማ ላይ አደጋ ለመጣል በምትዘምትበት ጊዜ በመጀመሪያ እንዲገብሩ የሰላም ድርድር ጠይቅ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምትበት ጊዜ፣ አስቀድመህ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምትበት ጊዜ፥ አስቀድመህ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለመዋጋት ወደ አንዲት ከተማ በደረስህ ጊዜ አስቀድመህ በሰላም ቃል ጥራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመዋጋት ወደ አንዲት ከተማ በደረስህ ጊዜ አስቀድመህ በዕርቅ ቃል ጥራቸው። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሠረገሎችን ከእስራኤል፥ የጦር ፈረሶችንም ከኢየሩሳሌም አስወግዳለሁ፤ የጦር ቀስቶችን እሰባብራለሁ፤ ንጉሥሽ በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲኖር ያደርጋል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርና ከታላቁ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይሆናል።”
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።
ከዚህ በኋላ ዮፍታሔ ወደ ዐሞን ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ “ከእኛ ጋር የተጣላህበት ምክንያት ምንድን ነው? አገራችንንስ የወረርከው ለምንድነው?” ብለው እንዲጠይቁት አደረገ።