የእስራኤል ሕዝብም “እኛ ከዋናው መንገድ አንወጣም፤ እኛ ወይም እንስሶቻችን ከውሃችሁ ብንጠጣ እንኳ ዋጋ እንከፍላችኋለን፤ እኛ የምንፈልገው በምድራችሁ አልፈን መሄድ ብቻ ነው” ሲሉ መለሱላቸው።
ዘዳግም 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያስፈልጋችሁን ምግብና ውሃ በገንዘብ ግዙ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ለምትበሉት ምግብም ሆነ ለምትጠጡት ውሃ በጥሬ ብር ትከፍሏቸዋላችሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፥ ውኃም ደግሞ በገንዘብ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገንዘብ በመለኪያ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገንዘብ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ። |
የእስራኤል ሕዝብም “እኛ ከዋናው መንገድ አንወጣም፤ እኛ ወይም እንስሶቻችን ከውሃችሁ ብንጠጣ እንኳ ዋጋ እንከፍላችኋለን፤ እኛ የምንፈልገው በምድራችሁ አልፈን መሄድ ብቻ ነው” ሲሉ መለሱላቸው።
እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፥ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው።
የኤዶምን ኮረብታማ አገር ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታኽል እንኳ አልሰጣችሁምና በእነርሱ ላይ ጦርነት አታንሡ።
“በእርግጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሠራችሁት ሥራ ሁሉ ብዙ በረከት ሰጥቶአችኋል፤ በዚህ በሰፊው በረሓ በሄዳችሁበት ሁሉ ተንከባክቦአችኋል፤ በእነዚህ በአርባ ዓመቶች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለ ነበረ ምንም የጐደለባችሁ ነገር አልነበረም።