ታዲያ እዚያ የምንሄደው ለምንድን ነው? እንፈራለን፤ የላክናቸውም ሰዎች በዚያ የሚኖሩት ሁሉ ብርቱዎችና በቁመታቸውም ከእኛ ይበልጥ ረጃጅሞች መሆናቸውን፥ እንዲሁም ርዝመታቸው እስከ ሰማይ የሚደርስ የግንብ ቅጽሮች ባሉአቸው ከተሞች የሚኖሩ መሆናቸውን ነገሩን፤ እጅግ ግዙፋን የሆኑ የዔናቅ ልጆችንም አይተዋል።’
ዘዳግም 2:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንደ ዐናቃውያን ቁመተ ረጃጅሞች፥ ብርቱና ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኀይል ዐሞናውያን ስለ ደመሰሱአቸው ምድራቸውን ወርሰው ራሳቸው ሰፍረውበት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘምዙማውያን ብርቱዎች፣ ቍጥራቸው የበዛና እንደ ዔናቃውያን ቁመተ ረዣዥሞች ነበሩ፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ፊት አጠፋቸው፤ እነርሱም አሳደዷቸው፤ በምትካቸውም ሰፈሩበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቅና ብዙም ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው የረዘመ ነበሩ፥ ጌታ ከፊታቸው አጠፋቸው፥ እነርሱንም ቀምተዋቸው በስፍራቸው ተቀመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም እንደ ዔናቃውያን ታላቅና ብዙ፥ ጽኑዓንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ከፊታቸው አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቅና ብዙም ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው የረዘመ ነበሩ፤ እግዚአብሔር ከፊታቸው አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ። |
ታዲያ እዚያ የምንሄደው ለምንድን ነው? እንፈራለን፤ የላክናቸውም ሰዎች በዚያ የሚኖሩት ሁሉ ብርቱዎችና በቁመታቸውም ከእኛ ይበልጥ ረጃጅሞች መሆናቸውን፥ እንዲሁም ርዝመታቸው እስከ ሰማይ የሚደርስ የግንብ ቅጽሮች ባሉአቸው ከተሞች የሚኖሩ መሆናቸውን ነገሩን፤ እጅግ ግዙፋን የሆኑ የዔናቅ ልጆችንም አይተዋል።’
[ይህም ግዛት በዚያ ይኖሩ በነበሩ ሕዝብ ይጠሩ በነበሩበት ስም የረፋያውያን ምድር ተብሎ ይጠራ ነበር፤ ዐሞናውያን በበኩላቸው ዛምዙሚም ብለው ይጠሩአቸው ነበር።
እግዚአብሔር ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም ለሚኖሩት ለዔሳው ዘሮችም እንደዚሁ አድርጎላቸው ነበር፤ ይኸውም ቀድሞ የኖሩባትን ሖራውያንን ደምስሶ እስከ አሁን የሚኖሩባትን ምድራቸውን ኤዶማውያን ወርሰው እንዲሰፍሩባት አድርጎአል።
ከረፋያውያን ወገን ንጉሥ ዖግ የመጨረሻው ነበር፤ አልጋው ከብረት የተሠራ ሆኖ በይፋ በታወቀው መለኪያ ቁመቱ አራት ሜትር፥ የጐኑም ስፋት ሁለት ሜትር ያኽል ነበር። እርሱም ራባ ተብላ በምትጠራው በዐሞናውያን ከተማ እስከ አሁን ይታያል።