ዘዳግም 18:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእህልህ፥ ከወይን ጠጅህና ከወይራ ዘይትህ ከተሸለቱ በጎችህም ጠጒር እንኳ ሳይቀር የመጀመሪያውን በኲራት ስጣቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእህልህን፣ የአዲሱን ወይንህንና የዘይትህን በኵራት እንዲሁም ከበጎችህ በመጀመሪያ የተሸለተውን ጠጕር ትሰጣለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእህልህን፥ የአዲሱን ወይንህንና የዘይትህን በኵራት እንዲሁም ከበጎችህ በመጀመሪያ የተሸለተውን ጠጉር ትሰጣለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእህልህን፥ የወይንህን፥ የዘይትህንም ቀዳምያት፥ አስቀድሞም የተሸለተውን የበግህን ጠጕር ለእርሱ ትሰጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእህልህን የወይን ጠጅህን የዘይትህንም በኩራት፥ አስቀድሞም የተሸለተውን የበግህን ጠጉር ለእርሱ ትሰጣለህ። |
“በየዓመቱ ከምታመርቱት ምርት መጀመሪያ የደረሰውን በኲራት ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ። “የበግን ወይም የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ እግዚአብሔር ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከር በምታጭዱበት ጊዜ የመጀመሪያውን ነዶ ለካህኑ ስጡ፤
እያንዳንዱ ቤተሰብ ሁለት እንጀራ በመወዝወዝ ልዩ መባ አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ እያንዳንዱ እንጀራ እርሾ ገብቶበት ከሁለት ኪሎ የላመ ዱቄት ጋር ተጋግሮ ስለሚሰበሰበው አዲስ መከር ለእግዚአብሔር የበኲራት መባ ሆኖ ይቅረብ።
ነገር ግን በመቃተት ላይ ያለው ፍጥረት ብቻ አይደለም፤ የመጀመሪያውን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ የተቀበልን እኛም የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን የእግዚአብሔር ልጆች መሆንን በተስፋ እየተጠባበቅን በውስጣዊ ሰውነታችን በመቃተት ላይ እንገኛለን፤