ዘዳግም 16:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋውን ቀቅለህ እግዚአብሔር አምላክህ በሚመርጠው ቦታ ብላው፤ በማግስቱ ወደ ድንኳኖችህ ተመለስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋውንም ጠብሰህ አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ብላ፤ ሲነጋም ወደ ድንኳንህ ተመልሰህ ሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋውን ቀቅለህ አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ቦታ ብላው፤ በማግስቱ ወደ ድንኳኖችህ ተመለስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ትጠብሰዋለህ፤ ታበስለዋለህም፤ ትበላውማለህ፤ በነጋውም ተመልሰህ ወደ ቤትህ ትሄዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ታበስለዋለህ፥ ትበላውማለህ፤ በነጋውም ተነሥተህ ወደ ድንኳንህ ትሄዳለህ። |
ሌዋውያኑም በሕጉ መሠረት የፋሲካውን መሥዋዕት በእሳት ጠበሱት፤ የተቀደሰውንም ቊርባን በምንቸት፥ በሰታቴና በድስት ቀቅለው ሥጋውን በፍጥነት ለሕዝቡ አከፋፈሉ፤
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤
ነገር ግን የመሥዋዕቱን እንስሳ የምታርደው እግዚአብሔር አምላክህ ለስሙ መጠሪያ በመረጠው ስፍራ ብቻ ነው። ይኸውም ፀሐይ ስትጠልቅ ከግብጽ በወጣህበት ቀን የወጣህበትን ሰዓት በመጠበቅ ነው።