የባዕዳን አገር ሕዝቦች በሰንበት ቀን ወይም በሌሎች በዓላት እህልም ሆነ ሌላ የንግድ ሸቀጥ ይዘው ቢመጡ፥ ከእነርሱ አንገዛም። በየሰባት ዓመት አንድ ጊዜ ምድሪቱን አናርስም፤ ያበደርነውንም ዕዳ ሁሉ እንሰርዛለን።
ዘዳግም 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አፈጻጸሙም እንደሚከተለው ነው፤ ለእስራኤላዊ ወገኑ ገንዘብ ያበደረ ሁሉ ያበደረውን ብድር ይሰርዝለት፤ እግዚአብሔር የዕዳ መሰረዣ ዓመት ነው ብሎ ያወጀበት ዓመት ስለ ሆነ ከእስራኤላዊ ወገኑ ያበደረውን ገንዘብ ለመቀበል አይፈልግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፈጻጸሙም እንደሚከተለው ነው፤ እያንዳንዱ አበዳሪ ለእስራኤላዊ ባልንጀራው ያበደረውን ይተውለት፤ እግዚአብሔር የዕዳ ምሕረት ዐውጇልና፣ አበዳሪው፣ እስራኤላዊ ባልንጀራውን ወይም ወንድሙን ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፈጻጸሙም የሚከተለው ነው፦ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፥ ጌታ የዕዳ ምሕረት አውጆአልና፥ ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምሕረቱም የሚገባ ትእዛዝ ይህ ነው፤ ባልንጀራህ ወይም ወንድምህ የሚከፍልህን ገንዘብ ሁሉ አትከፈል፤ የአምላክህ የእግዚአብሔር ምሕረት ተብላለችና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምሕረቱም የሚገባ ወግ ይህ ነው፤ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፤ የእግዚአብሔር ይቅርታ ታውጆአልና ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ አይሻ። |
የባዕዳን አገር ሕዝቦች በሰንበት ቀን ወይም በሌሎች በዓላት እህልም ሆነ ሌላ የንግድ ሸቀጥ ይዘው ቢመጡ፥ ከእነርሱ አንገዛም። በየሰባት ዓመት አንድ ጊዜ ምድሪቱን አናርስም፤ ያበደርነውንም ዕዳ ሁሉ እንሰርዛለን።
ሕዝቡም “እነሆ እኛ እንጾማለን፤ አንተ ግን አትመለከተንም፤ የማትመለከተንስ ከሆነ ሰውነታችንን ለምን እናዋርዳለን?” ይላሉ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “እነሆ እናንተ በምትጾሙበት ጊዜ የልባችሁን ፈቃድ ትፈጽማላችሁ፤ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ትጨቊናላችሁ፤
ሁለቱም የተበደሩትን መክፈል ቢያቅታቸው አበዳሪው ዕዳቸውን ተወላቸው፤ ታዲያ፥ ከሁለቱ ባለዕዳዎች፥ አበዳሪውን አብልጦ የሚወድ የትኛው ይመስልሃል?” አለው።
ለውጪ አገር ሰው ያበደርከው ብድር እንዲመለስልህ መጠየቅ ትችላለህ፤ ለማንኛውም እስራኤላዊ ወገንህ ያበደርከው ገንዘብ ግን እንዲመለስልህ መጠየቅ የለብህም።