ዘዳግም 14:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በውሃ ውስጥ የሚገኘው ክንፍና ቅርፊት የሌለው ፍጥረት ሁሉ አይበላም፤ እንደነዚህ ያሉት እንስሶች በእናንተ ዘንድ የረከሱ ሆነው መቈጠር አለባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክንፍና ቅርፊት የሌለውን ግን አትብሉ፤ ለእናንተ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክንፍና ቅርፊትም የሌለውን ግን አትብሉ፤ ለእናንተ ርኩስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸውን አትበሉም፤ ለእናንተ ርኩሳን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸውን አትበሉም፤ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። |
ማንም ሰው ንጹሕ ያልሆነው ከሰው ወይም ከእንስሶች የሚወጣ ማንኛውንም ርኩስ ነገር ነክቶ ይህን የአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ያ ሰው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ይለይ። ”