ዘዳግም 13:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላካችሁ በፍጹም ልባችሁ ትወዱት እንደ ሆነ ለማወቅ ፈልጎ ልኮት ይሆናልና ያን ነቢይ ወይም አላሚ አትስሙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁ ነውና፣ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም ዐላሚውን አትስማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላካችሁን ጌታ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ ጌታ ሊፈትናችሁ ነውና፥ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም አላሚውን አትስሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደሆን ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስማ። |
በመከራ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ ጠራችሁኝ፤ እኔም አዳንኳችሁ፤ ከመሰወሪያ ስፍራዬ፥ ከሞገድ ውስጥ ሰማኋችሁ፤ በክርክር ምንጮች አጠገብ ፈተንኳችሁ።
ሙሴም “አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሁኔታ ወደ እናንተ የመጣው ሊፈትናችሁና እርሱን በመፍራት ኃጢአት ከመሥራት ርቃችሁ እንድትኖሩ ነው” ሲል መለሰላቸው።
ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ እነርሱ ቢቻላቸውስ የእግዚአብሔርን ምርጦች እንኳ ለማሳሳት ታላላቅ ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።
በቤርያ ያሉት አይሁድ በተሰሎንቄ ካሉት ይልቅ ቅን አመለካከት ያላቸው ስለ ነበሩ ቃሉን በታላቅ ደስታ ተቀበሉ፤ የቃሉንም እውነተኛነት ለማረጋገጥ በየቀኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይመረምሩ ነበር።
ታዲያ፥ ይህን የምላችሁ በማዘዝ አይደለም፤ ነገር ግን የሌሎችን የመስጠት ትጋት ከእናንተ ትጋት ጋር በማወዳደር የእናንተን ፍቅር እውነተኛነት ለማረጋገጥ ብዬ ነው።
ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች የተንኰል ሽንገላና አታላይነት በተዘጋጀ በአሳሳች የትምህርት ነፋስና ሞገድ ወዲያና ወዲህ ተገፍትረው እንደሚወሰዱ ሕፃናት አንሆንም።
አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።
እነርሱ የወጡት ከእኛ መካከል ነው። ይሁን እንጂ ዱሮውንም ከእኛ ወገን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋርም ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን አለመሆናቸው እንዲታወቅ ከእኛ መካከል ተለይተው ወጥተዋል።
ወዳጆች ሆይ! በዓለም ላይ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ስለ ተነሡ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ይልቅስ መንፈሶች የእግዚአብሔር መሆናቸውንና አለመሆናቸውን መርምሩ።
ልጆች ሆይ! እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ፤ በእናንተ ያለው መንፈስ በዓለም ካለው መንፈስ ይበልጣል። ስለዚህ ሐሰተኞች ነቢያትን አሸንፋችኋል።
በመጀመሪያው አውሬ ፊት እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተአምራት ምክንያት በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር፤ በሰይፍ ቈስሎ ለዳነው ለአውሬው ክብር ምስል እንዲሠሩም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዛቸዋል።
እንዲያውም እነዚህ የእስራኤል ሕዝብ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው መንገዴን ይከተሉ ወይም አይከተሉ እንደሆን የማውቀው በእነዚህ ሕዝቦች መሣሪያነት በመፈተን ነው።”
ንጉሥ ሆይ! የምልህን አድምጠኝ! አንተን በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፥ መሥዋዕት በማቅረብ ቊጣውን እንዲመልስ ማድረግ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ ሄደህ ባዕዳን አማልክትን አምልክ ብለው እግዚአብሔር ከሰጠኝ ርስት ድርሻ ስላባረሩኝ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ።