ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ባዕሻ ራሱ ኃጢአት በመሥራትና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራት እግዚአብሔርን አሳዘነ።
ዘዳግም 12:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቃጠል መሥዋዕትህን በማናቸውም ቦታ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በፈለግኸው ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በፈለግኸው ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በሚታይህ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በሚታይህ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። |
ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ባዕሻ ራሱ ኃጢአት በመሥራትና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራት እግዚአብሔርን አሳዘነ።
ምንም እንኳ አሳ በኰረብቶቹ ላይ የነበሩትን የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ ባይደመስሳቸው፥ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነ፤
ከዚያም እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ የምታመጡት እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ መጠሪያ ወደ መረጠው ቦታ ይሆናል፤ ይኸውም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትን የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን ሁሉ ታመጡለታላችሁ።
መሥዋዕትህን ሁሉ ማቅረብ የሚገባህ ከነገዶችህ መካከል የአንዱ ግዛት በሆነው ክፍል እና እግዚአብሔር በሚመርጠው በአንድ ስፍራ ብቻ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህንም ሆነ ሌላውንም እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ በዚያ ስፍራ ብቻ ትፈጽማለህ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤
እዚያም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትንና የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን፥ የከብቶቻችሁንና የበጎቻችሁን በኲር ታቀርባላችሁ፤
እኛ በእግዚአብሔር ላይ አላመፅንም፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የእህል መባ፥ ወይም ሌላ መሥዋዕት ለማቅረብ አስበን ሌላ መሠዊያ በመሥራት እግዚአብሔርን ማምለክ አልተውንም፤ ከእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቆመው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ከተሠራው ሌላ የተለየ መሠዊያ መሥራት ከእኛ ይራቅ።”