ዘዳግም 11:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንድትኖሩባት የሰጣችሁን ምድር ለመውረስ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁና ወርሳችሁም በምትኖሩባት ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ምድር ትገቡባትና ትወርሷት ዘንድ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ስለ ሆነ፣ ምድሪቱን ወርሳችሁ በምትኖሩባት ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላካችሁ ጌታ በሚሰጣችሁ ምድር ትገቡባትና ትወርሷት ዘንድ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ስለሆነ፥ ምድሪቱን ወርሳችሁ በምትኖሩባት ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁ እግዚአብሔር በዕጣችሁ ለሁልጊዜ የሚሰጣችሁን ምድር ትገቡና ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፤ ትወርሱአታላችሁም፤ ትቀመጡባታላችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፥ ትወርሱአታላችሁም፥ ትቀመጡባታላችሁም። |
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አድምጥ፤ ከአንተ የሚበልጡትንና በኀይልም ብርቱ የሆኑትን የአሕዛብ ምድርና ቅጽሮቻቸው እስከ ሰማይ የደረሱ ታላላቅ ከተሞቻቸውን ለመውረስ ትገባ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገራለህ።
“ወደ ሰፈር ሄዳችሁ ለሕዝቡ እንዲህ ብላችሁ ንገሩ፦ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወርሱአት የሚሰጣችሁን ምድር ለመውረስ ከሦስት ቀን በኋላ ዮርዳኖስን ስለምትሻገሩ ስንቃችሁን አዘጋጁ።’ ”
ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል የገባላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤላውያን ሰጠ። ምድሪቱንም ከወረሱ በኋላ በዚያ ተደላድለው ኖሩ፤