ዘዳግም 11:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህም እኔ የሰጠኋችሁን ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውደዱ፤ በእርሱ መንገድም በመጓዝ ለእርሱ ታማኞች ሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፣ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከርሱም ጋራ ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላካችሁን ጌታን ትወዱ ዘንድ፥ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እርሱንም ትከተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቁ ብታደርጉአትም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቁ ብታደርጉአትም፥ |
እርሱም ሄዶ እግዚአብሔር ጸጋውን ለሕዝቡ እንዴት እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉም በሙሉ ልብ ጸንተው ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲኖሩም መከራቸው።
እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች ሁሉ በመፈጸም እግዚአብሔር አምላክህን ብትወድና በመንገዱ ብትሄድ ይህችን ምድር ስለሚሰጥህ ሌሎች ሦስት የመጠለያ ከተሞች ጨምረህ ሥራ።
አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ለእርሱም ታዛዥ ሁን፤ በእርሱም እመን፤ ይህም ለአንተ ሕይወት ከመሆኑም በላይ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል በገባላቸው መሠረት ገብተህ በምትኖርባት ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራለህ።”
ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ይህንንም አክሊል ያ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጁ ጌታ በዚያን ቀን ይሰጠኛል፤ የሚሰጠውም ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእርሱን መገለጥ ለሚወድዱ ሁሉ ነው።