ነገር ግን ኀይሉ በገነነ ጊዜ መንግሥቱ ይፈርስና በአራት የዓለም ማእዘን ይከፈላል፤ በቦታውም የእርሱ ዘሮች ያልሆኑ ነገሥታት ይተካሉ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ አንዱ እንኳ የእርሱን ያኽል ኀይል አይኖረውም፤ ይህም የሚሆነው ያ መንግሥት ፈርሶ እንደገና ለሌሎችም ስለሚከፋፈል ነው።
ዳንኤል 8:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ቀንድ ሲሰበር የወጡት አራት ቀንዶች ያ መንግሥት ለአራት መከፈሉን ያመለክታሉ፤ እያንዳንዱም መንግሥት የመጀመሪያውን መንግሥት ያኽል ብርቱ አለመሆኑን ይገልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተሰበረውን ቀንድ የተኩት አራቱ ቀንዶች፣ ከመንግሥቱ የሚወጡትን አራት መንግሥታት ያመለክታሉ፤ ነገር ግን በኀይል አይተካከሉትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም በተሰበረ ጊዜ በእርሱ ፋንታ አራቱ እንደ ተነሡ፥ እንዲሁ ከወገኑ አራት መንግሥታት ይነሣሉ፥ ነገር ግን በኃይል አይተካከሉትም። |
ነገር ግን ኀይሉ በገነነ ጊዜ መንግሥቱ ይፈርስና በአራት የዓለም ማእዘን ይከፈላል፤ በቦታውም የእርሱ ዘሮች ያልሆኑ ነገሥታት ይተካሉ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ አንዱ እንኳ የእርሱን ያኽል ኀይል አይኖረውም፤ ይህም የሚሆነው ያ መንግሥት ፈርሶ እንደገና ለሌሎችም ስለሚከፋፈል ነው።
“ይህንን በመመልከት ላይ ሳለሁ እነሆ፥ ሌላ ነብር የሚመስል አውሬ ወጣ፤ እርሱም የወፍ ክንፎች የሚመስሉ አራት ክንፎች በጀርባው ላይ ነበሩት፤ አራት ራሶችም ነበሩት፤ የገዢነት ሥልጣንም ተሰጠው።
“ከዚያ በኋላ አራተኛውን አውሬ አየሁ፤ እርሱም አስፈሪ፥ አስደንጋጭና በጣም ኀይለኛ ነበር፤ ይህም አውሬ የሚቦጫጭቅባቸውና የሚሰባብርባቸው ታላላቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት። የተረፈውንም በእግሮቹ ይረግጠው ነበር፤ ካለፉትም አውሬዎች ሁሉ የተለየ ሆኖ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።
በዚያም ወንዝ ዳር ሁለት ረጃጅም ቀንዶች ያሉት አንድ አውራ በግ ቆሞ ነበር፤ ከሁለቱ ቀንዶች አንደኛው ዘግይቶ የበቀለ ቢሆንም ከሌላው ቀንድ ይረዝም ነበር።
አውራው ፍየል እጅግ እየበረታ ሄደ፤ ከኀያልነቱም የተነሣ ታላቅ የነበረው ቀንዱ ተሰበረ፤ በቦታውም አራት ታላላቅ ቀንዶች ተተኩ፤ እያንዳንዱም ቀንድ ወደተለያየ አራት አቅጣጫ ያመለክት ነበር፤