እነዚህ ሁለቱም ነገሮች በቅጽበት በአንድ ቀን በአንቺ ላይ ይደርሳሉ፤ ምንም ያኽል መተትሽ ትልቅ፥ ጥንቈላሽም ብዙ ቢሆን የልጆችና የባል ሞት በአንቺ ላይ በሙላት ይደርሳል።
ዳንኤል 5:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ሌሊት የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር ተገደለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ሌሊት የባቢሎናውያን ንጉሥ ቤልሻዛር ተገደለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ሌሊት የከለዳውያን ንጉሥ ብልጣሶር ተገደለ። |
እነዚህ ሁለቱም ነገሮች በቅጽበት በአንድ ቀን በአንቺ ላይ ይደርሳሉ፤ ምንም ያኽል መተትሽ ትልቅ፥ ጥንቈላሽም ብዙ ቢሆን የልጆችና የባል ሞት በአንቺ ላይ በሙላት ይደርሳል።
የእግዚአብሔር ዓላማ ስለ ቤተ መቅደሱ የበቀል ዕርምጃ ለመውሰድ ስለ ሆነ ባቢሎንን ለማጥፋት የሜዶንን ነገሥታት አነሣሥቶአል፤ ስለዚህ ፍላጻችሁን ሳሉ! ጋሻችሁንም አንሡ!
የእርሱ ከተማ ከዳር እስከ ዳር የተያዘች መሆንዋን ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንዱ ሩዋጭ ለሌላው ሩዋጭ፥ አንዱ መልእክተኛ ለሌላው መልእክተኛ መልእክቱን ለማስተላለፍ ይሯሯጣሉ።
ሞቅ ባላቸው ጊዜ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ፤ እስኪሰክሩ ድረስም አጠጣቸዋለሁ፤ ከዚያም ዘለዓለማዊ እንቅልፍ ያንቀላፋሉ፤ እስከ መቼም አይነቁም።
መሳፍንትዋ፥ የጥበብ ሰዎችዋ፥ መሪዎችዋ፥ የጦር አዛዦችዋና ወታደሮችዋ ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይተኛሉ፤ እስከ ዘለዓለም አይነቁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ንጉሡ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።