Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 5:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ከዚህም በኋላ ብልጣሶር ወዲያውኑ ዳንኤልን መጐናጸፊያ እንዲያለብሱት፥ የወርቅ ኒሻን በአንገቱ እንዲያደርጉለትና በመንግሥቱም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕርግ እንዲይዝ እንዲያደርጉት በዐዋጅ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ከዚህ በኋላ በቤልሻዛር ትእዛዝ ዳንኤልን ሐምራዊ መጐናጸፊያ አለበሱት፣ የወርቅ ሐብል በዐንገቱ ላይ አጠለቁለት፤ የመንግሥቱም ሦስተኛ ገዥ ሆኖ ተሾመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የዚያን ጊዜም ብልጣሶር ለዳንኤል ሐምራዊ ግምጃ እንዲያለብሱት፥ የወርቅ ማርዳም በአንገቱ ዙሪያ እንዲያደርጉለት አዘዘ፥ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዥ እንዲሆን አዋጅ አስነገረ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 5:29
7 Referencias Cruzadas  

ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።


አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ደረጃ ከንጉሥ አርጤክስስ ቀጥሎ ሁለተኛ ነበር፤ እርሱም በወገኖቹ በአይሁድ ዘንድ በጣም የተከበረና የተወደደ ሰው ነበር፤ መርዶክዮስ ለወገኖቹና ለዘሮቻቸው በሰላም የመኖር ዋስትና ለማስገኘት በብርቱ የደከመ ሰው ነበር።


እነርሱም ለራስህ ክብርን እንደሚያቀዳጅ ዘውድ፥ ለአንገትህም ውበትን እንደሚሰጥ ሐብል ይሆኑልሃል።


ከዚህ በኋላ ንጉሡ ዳንኤልን በታላቅ ክብር ቦታ አስቀመጠው፤ ብዙ ስጦታዎችንም ሰጠው፤ በባቢሎን ግዛትም ሁሉ ላይ የበላይ ገዢ አደረገው፤ በባቢሎንም ጠቢባን ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው።


አንተ ግን የተሰወረውን ነገር የመተርጐምና አስቸጋሪ የሆነውን ነገር ሁሉ የመፍታት ችሎታ እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ይህን ጽሕፈት አንብበህ ትርጒሙን ብትነግረኝ፥ ሐምራዊ መጐናጸፊያ እንድትለብስ፤ የወርቅ ኒሻን በአንገትህ እንድታደርግና በመንግሥቴም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕርግ እንድትይዝ አደርጋለሁ።”


አስማተኞችን፥ ጠንቋዮችንና ኮከብ ቈጣሪዎችን እንዲያስገቡለት በከፍተኛ ድምፅ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም ተጠርተው በመጡ ጊዜ ንጉሡ “ይህን ጽሕፈት አንብቦ ትርጒሙን ሊነግረኝ የሚችል ሰው፥ ሐምራዊ መጐናጸፊያ ይለብሳል፤ የወርቅ ኒሻንም ይደረግለታል፤ በመንግሥቴም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕርግ ይይዛል” አለ።


በተጨማሪም የንጉሡ ቅርብ ረዳቶች ሆነው ንጉሡ ምንም ነገር እንዳይጐድልበት አገረ ገዢዎቹን እንዲቈጣጠሩ ዳንኤልንና ሌሎችን ሁለት ሰዎች መረጠ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos