የዐዋጁም ቃል እንዲህ የሚል ነው፤ “ይህ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት የቂሮስ ትእዛዝ ነው፤ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ላይ ገዢ አድርጎኛል፤ በይሁዳ ውስጥ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ከተማ ለእርሱ ክብር ቤተ መቅደስን እሠራ ዘንድ ኀላፊነት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰዎች የሆናችሁ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሂዱ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሁን።”
ዳንኤል 5:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፋርስ ‘መንግሥትህ ተከፍሎ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ’ ማለት ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ፋሬስ ማለት መንግሥትህ ተከፈለ፣ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ ማለት ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፋሬስ ማለት፥ መንግሥትህ ተከፈለ፥ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው። |
የዐዋጁም ቃል እንዲህ የሚል ነው፤ “ይህ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት የቂሮስ ትእዛዝ ነው፤ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ላይ ገዢ አድርጎኛል፤ በይሁዳ ውስጥ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ከተማ ለእርሱ ክብር ቤተ መቅደስን እሠራ ዘንድ ኀላፊነት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰዎች የሆናችሁ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሂዱ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሁን።”
አስፈሪ የሆነ ራእይ ተገልጦልኛል፤ ይኸውም አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ከዳተኛው ይከዳል፤ ዘራፊውም ይዘርፋል። የዔላም ሠራዊት ሆይ! አደጋ ለመጣል ውጡ! የሜዶን ሠራዊት ሆይ! ከተሞችን ክበቡ! እግዚአብሔር በባቢሎን ምክንያት የደረሰውን ሥቃይ ሁሉ ያስወግዳል።
በመተትሽ ልታስወግጂ የማትችይው ክፉ ነገር ይመጣብሻል፤ ልትከላከዪ የማትችይው ችግር ይደርስብሻል፤ ምንም ያላሰብሽው ጥፋት በድንገት ያጋጥምሻል።
በኤርምያስ አማካይነት በሕዝብ ሁሉ ላይ አመጣለሁ ያልኩትን፥ ማለትም በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ሁሉ በላይዋ ላይ በማውረድ ባቢሎንን እቀጣለሁ።
ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ፤ መድቡ፤ ወደ ሜዶን ነገሥታት፥ ወደ መሪዎቻቸውና ጦር አዛዦቻቸው እንዲሁም እነርሱ በሚቈጣጠሩአቸው አገሮች ወደሚኖሩ ሠራዊት ሁሉ መልእክት ላኩ።
ከአንተ በኋላ በገናናነቱ የአንተን መንግሥት የሚያኽል አነስተኛ መንግሥት ይነሣል፤ ከእርሱም ቀጥሎ ዓለምን ሁሉ የሚገዛ በነሐስ የሚመሰል መንግሥት በሦስተኛ ደረጃ ይነሣል።