La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዳንኤል 4:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“አእምሮዬ እንደ ተመለሰልኝ ወዲያውኑ የመንግሥቴ ክብርና ግርማ ማዕርጉም ሁሉ እንደገና ተሰጠኝ፤ አማካሪዎቼና መኳንንቴ በደስታ ተቀበሉኝ፤ ከቀድሞው የበለጠ ክብር ተጨምሮልኝ በንጉሥነቴ ጸናሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አእምሮዬ እንደ ተመለሰልኝ፣ ወዲያው ለመንግሥቴ ክብር፣ ግርማዊነቴና ሞገሴ ተመለሱልኝ፤ አማካሪዎቼና መኳንንቴ ፈለጉኝ፤ ወደ ዙፋኔም ተመለስሁ፤ ከቀድሞውም የበለጠ ታላቅ ሆንሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያ ጊዜም አእምሮዬ ተመለሰልኝ፥ ለመንግሥቴም ክብር ግርማዬና ውበቴ ወደ እኔ ተመለሰ፥ አማካሪዎቼና መኳንንቶቼም ፈለጉኝ፥ በመንግሥቴም ውስጥ ጸናሁ፥ ብዙም ክብር ተጨመረልኝ።

Ver Capítulo



ዳንኤል 4:36
11 Referencias Cruzadas  

ምሳሌያዊ አነጋገራችሁ እንደ ዐመድ ዋጋ ቢሶች ናቸው፤ ክርክራችሁም እንደ ሸክላ ተሰባብሮ ይወድቃል።


እግዚአብሔርን መፍራትና ትሑት መሆን ሀብት፥ ክብርና ሕይወትን ያስገኛል።


“ንጉሥ ሆይ! እጅግ የሚያንጸባርቅና ብልጭልጭታው ለማየት የሚያስፈራ ታላቅ ምስል በፊትህ ቆሞ አየህ።


“ንጉሥ ሆይ! ረጅምና ብርቱ የሆነው ያ ዛፍ አንተ ነህ፤ ታላቅነትህ እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ብሎአል፤ ሥልጣንህም በዓለም ሁሉ ላይ ተንሰራፍቶአል።


ከሕዝብ መካከል ተባረህ መኖሪያህ ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ ይህም የሚሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ነው።”


ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “ሰባቱ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ቀና ብዬ ወደ ሰማይ ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤ ለዘለዓለማዊው አምላክ ክብርና ውዳሴ አቀረብኩ፤ “ግዛቱ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤


እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤


ይህም ቀላልና ጊዜያዊ የሆነ መከራችን ወደር የሌለውን እጅግ ታላቅ የሆነ ዘለዓለማዊ ክብር ያስገኝልናል።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የአንተ ቤተሰብና የቀድሞ አባትህ ቤተሰብ ለዘለዓለም ያገለግሉኝ ዘንድ ቃል ገብቼ ነበር፤ አሁን ግን እንዲህ አይሆንም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ የሚንቁኝም ይናቃሉ።