ዳንኤል 11:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ በሚያንሰራፋበትም ጊዜ ግብጽም ራስዋ አታመልጥም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ ያንሰራፋል፤ ግብጽም አታመልጥም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጁን በአገሮች ላይ ይዘረጋል፥ የግብጽም ምድር አታመልጥም። |
ውብ የሆነችውንም የተስፋይቱን ምድር ይወራል፤ ብዙ አገሮችም በእርሱ እጅ ይወድቃሉ፤ ነገር ግን የኤዶም፤ የሞአብና የዐሞን አገሮች ከወረራው ያመልጣሉ።
ሬሳቸውም በምሳሌያዊ አጠራር ሰዶም ወይም ግብጽ በምትባል በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይጋደማል፤ ይህች ከተማ የእነርሱ ጌታ የተሰቀለባት ናት።