Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 11:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 የግብጽን ወርቅ፤ ብርና ሌላውንም የከበረ ነገር ሁሉ ከተደበቀበት ቦታ ይወስዳል፤ ሊቢያንና ኢትዮጵያንም ድል ያደርጋል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 የወርቅና የብር ክምችትን፣ እንዲሁም የግብጽን ሀብት ሁሉ በቍጥጥሩ ሥር ያደርጋል፤ የሊቢያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይገዙለታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብጽ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል፥ የልብያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 11:43
9 Referencias Cruzadas  

እርሱም አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሠረገሎችና ሥልሳ ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሺሻቅ ጦር ሠራዊት ውስጥ ከእርሱ ጋር ከግብጽ የመጡ ብዛታቸው ሊቈጠር የማይቻል ሊቢያውያን፥ ሱካውያንና ኢትዮጵያውያን ነበሩ፤


ሙሴም “መኳንንትህ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው እጅ ይነሡኛል፤ ሕዝቤንም ይዤ እንድወጣ ይለምኑኛል፤ ከዚያም በኋላ እሄዳለሁ” በማለት ንግግሩን አበቃ፤ ይህንንም ከተናገረ በኋላ በታላቅ ቊጣ ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ሄደ።


ከፋርስ፥ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ የመጡ ሰዎችም ሁሉ ጋሻ አንግበው የራስ ቊር ደፍተው የእርሱ ተባባሪዎች በመሆን ከእርሱ ጋር ተሰልፈዋል።


ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ በሚያንሰራፋበትም ጊዜ ግብጽም ራስዋ አታመልጥም።


ከዚያን በኋላ ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣው ወሬ ያስደነግጠዋል፤ በታላቅ ቊጣ ተነሣሥቶ ብዙ ሰዎችን በማጥፋት እንዳልነበሩ ያደርጋል።


ወሰን የሌለው ኀይልዋ ከግብጽ ከራስዋና ከኢትዮጵያ ይመጣ ነበር፤ የፉጥና ሊብያ ሰዎችም ተባባሪዎችዋ ነበሩ።


ባራቅም የንፍታሌምንና የዛብሎንን ነገዶች ወደ ቃዴስ አስጠራ፤ ከእነርሱም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም አብራው ዘመተች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos