ዳንኤል 11:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሮማውያን በመርከብ መጥተው ስለሚወጉት በብርቱ ይደነግጣል፤ ወደ ኋላውም አፈግፍጎ በታላቅ ቊጣ ለአይሁድ የተሰጠውን የተቀደሰ ቃል ኪዳን ያረክሳል፤ ተመልሶም ሃይማኖታቸውን ከካዱት ሰዎች ጋር ይወዳጃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኪቲም መርከቦች ይቃወሙታል፤ ልቡም ይሸበራል። ወደ ኋላም ይመለሳል፤ ቍጣውን በተቀደሰው ኪዳን ላይ ያወርዳል፤ ተመልሶም የተቀደሰውን ኪዳን የተዉትን ይንከባከባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኪቲም መርከቦች ይመጡበታልና ስለዚህ አዝኖ ይመለሳል፥ በቅዱሱም ቃል ኪዳን ላይ ይቈጣል፥ ፈቃዱንም ያደርጋል፥ ተመልሶም ቅዱሱን ቃል ኪዳን የተዉትን ሰዎች ይመለከታል። |
በነገሩ ሳሰላስል፥ እርሱ እንዲህ ዐይነቱን የሐሰት ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠኝ ጦቢያና ሰንባላጥ በገንዘብ የደለሉት እንጂ ሸማዕያ ከእግዚአብሔር የተላከ ነቢይ አለመሆኑን ተገነዘብኩ።
ስለ ጢሮስ ከተማ የተነገረ የትንቢት ቃል ይህ ነው፤ ጢሮስና ቤትዋ ወይም ወደብዋ የፈራረሱ ስለ ሆነ እናንተ የተርሴስ መርከቦች እሪ በሉ፤ ከቆጵሮስ ስትመለሱ የሚጠብቃችሁ ወሬ ይኸው ነው።
“አንቺ የሲዶን ከተማ ሆይ! የደስታሽ ዘመን አክትሞአል፤ ሕዝብሽ ተጨቊነዋል፤ ወደ ቆጵሮስ ሸሽተው ቢያመልጡ እንኳ እዚያ በሰላም አይኖሩም” ብሎአል።
ይህን የመሰለ ነገር ከዚህ በፊት ከቶ ተደርጎ እንደማያውቅ ታስተውሉ ዘንድ፥ እስቲ በስተ ምዕራብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ሂዱ፤ በስተ ምሥራቅም ወደ ቄዳር ምድር መልእክተኞች ልካችሁ መርምሩ።
መቅዘፊያዎችሽ የተሠሩት ከባሳን በተገኘ የወርካ ዛፍ ነው፤ ወለልሽም የተሠራው ከቆጵሮስ በተገኘ ልዩ በሆነ የጥድ ሳንቃ ነው፤ ዙሪያውም በዝሆን ጥርስ ተለብጦአል።
የሶርያ ንጉሥ የማረከውን ሀብት ሁሉ ይዞ ይመለሳል፤ ልቡ ግን የተቀደሰውን ቃል ኪዳን ለማጥፋት ነው፤ የፈለገውን ሁሉ ካደረገ በኋላ ወደ አገሩ ይሄዳል።
በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።
ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ ዲያብሎስ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ምድርና ባሕር ወዮላችሁ!”