ከወደ ሰሜን የሚመጣው ወራሪ የፈለገውን ያደርጋል፤ እርሱን ቆሞ የሚመክት አይኖርም፤ እርሱ የተቀደሰችውን አገር እንኳ ሳይቀር ወሮ ይይዛታል።
ዳንኤል 11:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚያን በኋላ ጦረኛ የሆነ አንድ ብርቱ ንጉሥ ይነሣል፤ የመንግሥቱ ግዛት ታላቅ ይሆናል፤ የፈለገውንም ሁሉ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በታላቅ ኀይል የሚገዛና የወደደውንም ሁሉ የሚያደርግ ኀያል ንጉሥ ይነሣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃያልም ንጉሥ ይነሣል፥ በትልቅ አገዛዝም ይገዛል፥ እንደ ፈቃዱም ያደርጋል። |
ከወደ ሰሜን የሚመጣው ወራሪ የፈለገውን ያደርጋል፤ እርሱን ቆሞ የሚመክት አይኖርም፤ እርሱ የተቀደሰችውን አገር እንኳ ሳይቀር ወሮ ይይዛታል።
“የሶርያ ንጉሥ የፈለገውን ሁሉ ይፈጽማል፤ ራሱንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ባለው አምላክ ላይ ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማይታወቅ የስድብ ቃል ይናገራል፤ የታቀደው ሁሉ መደረግ ስላለበት የእግዚአብሔር የቊጣው ቀን እስኪደርስ ድረስ ይሳካለታል።
በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።
ከገናናነቱም የተነሣ በልዩ ልዩ አገሮች የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ሁሉ በፊቱ በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር፤ የፈለገውን መግደልና የፈለገውን ማዳን፥ የፈለገውን መሾምና ያልፈለገውን መሻር ይችል ነበር።
“ይህንን በመመልከት ላይ ሳለሁ እነሆ፥ ሌላ ነብር የሚመስል አውሬ ወጣ፤ እርሱም የወፍ ክንፎች የሚመስሉ አራት ክንፎች በጀርባው ላይ ነበሩት፤ አራት ራሶችም ነበሩት፤ የገዢነት ሥልጣንም ተሰጠው።
እግዚአብሔርም ደግሞ ምልክቶችን፥ ድንቅ ነገሮችን፥ ልዩ ልዩ ተአምራትን በማድረግና እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቸውን አጽንቶአል።