ዳንኤል 11:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ንጉሡ ወደ ገዛ አገሩ ምሽጎች ይመለሳል፤ ነገር ግን ተሰናክሎ ስለሚወድቅ ዳግመኛ አይታይም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገዛ አገሩ ወዳሉት ምሽጎችም ፊቱን ይመልሳል፤ ነገር ግን ተሰናክሎ ይወድቃል፤ ዳግምም አይታይም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊቱንም ወደ ገዛ ምድሩ አምባዎች ይመልሳል፥ ተሰናክሎም ይወድቃል፥ አይገኝምም። |
ምድር እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ በዐውሎ ነፋስ እንደ ተገፋ ጎጆም ትናወጣለች፤ እርስዋም የኃጢአትዋ ሸክም ስለሚጫናት ትወድቃለች፤ መነሣትም አትችልም።
መጨረሻሽ አስፈሪ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ፍጻሜሽ ይሆናል፤ ሰዎች ቢፈልጉሽ እንኳ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከቶ አያገኙሽም፤” እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ወዲያውኑ የእርስዋ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ይነግሣል፤ ከሶርያ ንጉሥ ሠራዊት ጋር ጦርነት ይገጥማል፤ ምሽጋቸውንም ሰብሮ በመግባት ድል ይነሣቸዋል።