ዳንኤል 10:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀና ብዬ ስመለከት ቀጭን ሐር የለበሰና በወገቡም የወርቅ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀና ብዬ ስመለከት፣ በፊቴ በፍታ የለበሰና በወገቡም ላይ የአፌዝ ወርቅ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ። |
ምስሎቻቸው ከተርሴስ በመጣ ጥሬ ብርና ከኡፋዝ በተገኘ ወርቅ ተለብጠዋል፤ በብልኀተኞችም ሥራ አጊጠዋል፤ ጥበበኞች ሸማኔዎች በሠሩአቸውም የወይን ጠጅና ሐምራዊ ልብስ ተሸፍነዋል።
ስድስት ሰዎችም የመግደያ መሣሪያዎቻቸውን ይዘው ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መጡ፤ ከእነርሱም መካከል በፍታ የለበሰና የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር በጐኑ የያዘ አንድ ሰው ነበር። ስድስቱም ሰዎች ገብተው በነሐሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
የእግዚአብሔር መልአክ በቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አየሁ። እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆመ፤ በስተኋላውም ቀይ፥ ሐመርና አምባላይ ፈረሶች ይከተሉት ነበር።
ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ሰይፍ የያዘ አንድ ጐልማሳ በድንገት በፊቱ ቆሞ ታየው፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “አንተ የእኛ ወገን ነህ ወይስ የጠላቶቻችን?” አለው።