አሞጽ 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከአንዲት የእስራኤል ከተማ ሺህ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ በሕይወት የሚቀሩት ግን አንድ መቶ ብቻ ይሆናሉ፤ ከሌላይቱም ከተማ መቶ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ ተመልሰው የሚመጡት ግን ዐሥር ብቻ ይሆናሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ ሺሕ ብርቱዎችን ለእስራኤል የምታዘምት ከተማ፣ አንድ መቶ ብቻ ይቀሯታል፤ አንድ መቶ ብርቱዎችን የምታዘምተውም፣ ዐሥር ብቻ ይቀሯታል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፦ “ሺህ ከሚወጣበት ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ከሚወጣባት ከተማ ለእስራኤል ቤት ዐሥር ይቀርላታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፥ “ሺህ ከሚወጡባት ከተማ መቶ ይቀራሉ፤ መቶም ከሚወጡባት ከተማ ለእስራኤል ቤት ዐሥር ይቀራሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፦ ሺህ ከሚወጣበት ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ከሚወጣባት ከተማ ለእስራኤል ቤት አሥር ይቀርላታል። |
ምንም እንኳ የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ቢሆንም ከእነርሱ መካከል የሚድኑት የተረፉት ብቻ ናቸው፤ ለሕዝቡ ጥፋት ተገቢ የሆነ እውነተኛ ፍርድ ተዘጋጅቶአል።
ከዐሥሩ አንድ ክፍል ቢተርፍም እንኳ እርሱም እንደ ግራር ወይም እንደ ዋርካ እንደገና ይቃጠላል። ዛፉ ሲቈረጥ ጉቶው ይቀራል። ጉቶውም የተቀደሰ ዘር ነው።”
ነገር ግን ከእነርሱ ጥቂቶቹን ከጦርነት፥ ከራብና ከቸነፈር እንዲተርፉ አደርጋለሁ፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቦች መካከል ሲኖሩ ሥራቸው ምን ያኽል አጸያፊ እንደ ነበር ይገነዘባሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ “የእስራኤል ልጆች ቊጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢበዛ እንኳ ከእነርሱ የሚድኑት ጥቂቶች ብቻ ናቸው።
እግዚአብሔር እናንተን ለማበልጸግና ቊጥራችሁንም ለማብዛት እንደ ወደደው ሁሉ እንደገናም እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስ ደስ ይለዋል። ከዚህች ከምትወርሱአት ምድር ተነቃቅላችሁ ትጠፋላችሁ።