“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፥ እንዲሁም በውርጭ በዋግና በአንበጣ ወይ በኩብኩባ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ፥ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ፥ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፥
አሞጽ 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰብላችሁን የሚያደርቅ ብርቱ ነፋስ ላክሁባችሁ፤ አትክልታችሁንና የወይን ተክላችሁን የበለስና የወይራ ዛፋችሁን ሁሉ አንበጣ በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤ በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤ አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፤ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአባርና በቸነፈር መታኋችሁ፤ አትክልታችሁ፥ ወይናችሁና በለሳችሁ፥ ወይራችሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እናንተ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፥ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በልቶአል፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። |
“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፥ እንዲሁም በውርጭ በዋግና በአንበጣ ወይ በኩብኩባ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ፥ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ፥ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፥
“በምድሪቱ ላይ ራብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፥ እንዲሁም የእህል ሰብል በሚያቃጥል ነፋስና በአንበጣ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ፥ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብህ ላይ ከበባ በሚያደርጉበት ጊዜ፥ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፥
እናንተ ሁላችሁም ነገር በሰው ላይ እንደ እሳት የምታነዱና እንደ ችቦ የምትለኲሱ ናችሁ፤ ባነደዳችሁት እሳት ነበልባል ውስጥና በለኰሳችሁት ችቦ ትጠፋላችሁ ይህንንም ቅጣት የምትቀበሉት ከእኔ ነው።
እርሱ ከምሥራቅ ሶርያውያንን፥ ከምዕራብ ፍልስጥኤማውያንን ልኮ እስራኤልን እንዲወሩ አደረገ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ቊጣው አልበረደም፤ ስለዚህ እጁ እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተቃጣ ነው።
ይህን ሁሉ ከፈጸመች በኋላ እምነት የማይጣልባት የእስራኤል እኅት የሆነችው ይሁዳ፥ እንደገና ወደ እኔ ለመመለስ የምትሞክር መስላ የታየችው ከልብዋ ሳይሆን ከአንገት በላይ ነበር፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
ከተምች መንጋ የተረፈውን ሰብል፥ የሚርመሰመስ የአንበጣ መንጋ በላው፤ ከዚያ የተረፈውን እንደ ውሽንፍር የሚገርፍ የአንበጣ መንጋ አጠፋው፤ ከዚያም የተረፈውን ኲብኲባ በላው።
ለዘመናት እንደ ትልቅ ሠራዊት የላክሁባችሁ እንደ ውሽንፍር የሚገርፉ አንበጦች፥ ኲብኲባዎች፥ ተምቾችና የሚርመሰመሱ አንበጦች የፈጁባችሁን ሰብል እተካላችኋለሁ።
ሰዎች ውሃ መጠጣት ፈልገው ከከተማ ወደ ከተማ ሄዱ፤ ነገር ግን በቂ ውሃ ባለማግኘታቸው ጠጥተው ሊረኩ አልቻሉም፤ እናንተም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፥ በወይን ተክል ላይም ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ዛፍም ምንም ፍሬ ባይሰጥ፥ በእርሻዎች ላይ ሰብል ቢጠፋ፥ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፥ በበረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፥
እግዚአብሔር በሚያመነምን በሽታ፥ በትኲሳት፥ በቊስል፥ በኀይለኛ ሙቀትና በድርቅ እስክትጠፋም ድረስ ይመታሃል። ሰብልህንም ለማጥፋት ዋግና አረማሞ ይልክብሃል።