ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል” ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
ሐዋርያት ሥራ 7:58 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከከተማ አወጡትና በድንጋይ ወገሩት፤ ምስክሮችም ልብሳቸውን ወስደው ሳውል የሚባል አንድ ጐልማሳ እንዲጠብቅላቸው በእግሩ ሥር አስቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይዘውም ከከተማው ውጭ ጣሉት፤ በድንጋይም ይወግሩት ጀመር። ይህ በሚሆንበት ጊዜ በዚያ የነበሩ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በተባለ ጕልማሳ እግር አጠገብ አስቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከከተማም ወደ ውጭ ጐትተው አውጥተው ወገሩት፤ የሚወግሩት ሰዎችም ልብሳቸውን ሳውል በሚባል ጐልማሳ እግር አጠገብ አስቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ። |
ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል” ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
ተነሥተውም ኢየሱስን ጐትተው ከከተማ ውጪ አወጡት፤ ወደ ገደልም ገፍትረው ሊጥሉት ፈልገው ከተማቸው ወደ ተሠራችበት ኰረብታ አፋፍ ላይ ወሰዱት።
የአንተ ምስክር የነበረው እስጢፋኖስ በተገደለ ጊዜ እኔም ራሴ በገዳዮቹ አጠገብ ቆሜ ከእነርሱ ጋር በነገሩ ተስማምቼ ነበር፤ ልብሳቸውንም እጠብቅ ነበር፤’
የክርስትናን እምነት የሚከተሉትን ሁሉ እስከ ሞት የማሳድድ ሰው ነበርኩ፤ ወንዶችንና ሴቶችን እያሰርኩ ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ አደርግ ነበርኩ።
በኢየሩሳሌም ያደረግኹትም ይህንኑ ነበር፤ ከካህናት አለቆች በተቀበልኩት ሥልጣን ከምእመናን ብዙዎቹ ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ አድርጌአለሁ፤ ሲገድሉአቸውም ከገዳዮቻቸው ጋር ተስማምቻለሁ።
በእርሱ ላይ በሐሰት የሚመሰክሩ አንዳንድ ሰዎችንም አመጡ፤ የሐሰት ምስክሮችም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅደስና በሕግ ላይ የስድብ ቃል ከመናገር አይቈጠብም።
ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር፤ እስጢፋኖስ በሞተበት ቀን በኢየሩሳሌም በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያት በቀር አማኞች ሁሉ ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ ምድር ተበተኑ።
ምስክሮቹ የመጀመሪያዎቹን ድንጋዮች ይወርውሩ፤ ከዚያም ቀጥሎ ሌላው ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው፤ በዚህም ዐይነት እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ሁሉ ከመካከልህ ታስወግዳለህ።