ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኀይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ፤
ሐዋርያት ሥራ 7:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሙሴ በዚያ አገር አርባ ዓመት ካሳለፈ በኋላ በደብረ ሲና በረሓ በሚነደው የቊጥቋጦ ነበልባል ውስጥ አንድ መልአክ ታየው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከአርባ ዓመት በኋላ፣ በሲና ተራራ አካባቢ ባለው ምድረ በዳ፣ በቍጥቋጦው ውስጥ በሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል መልአክ ተገለጠለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አርባ ዓመትም ሲሞላ የጌታ መልአክ በሲና ተራራ ምድረ በዳ በቁጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አርባ ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ በበረሃ በደብረ ሲና የእግዚአብሔር መልአክ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አርባ ዓመትም ሲሞላ የጌታ መልአክ በሲና ተራራ ምድረ በዳ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው። |
ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኀይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ፤
እኔ የቀድሞ አባቶችህ የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤” በዚህ ጊዜ ሙሴ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ።
በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።
በችግራቸው ጊዜ ሁሉ ያዳናቸው በመልእክተኛ ወይም በመልአክ አማካይነት ሳይሆን እርሱ በመካከላቸው በመገኘት ነው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ታደጋቸው፤ እርሱም በቀድሞ ዘመናት ሁሉ አንሥቶ ልጁን እንደሚሸከም ሰው ተንከባከባቸው።
ከዚህ በኋላ አገረ ገዢዎቹ፥ መኳንንቱ፥ አማካሪዎቹ ሁሉ በእነርሱ ዙሪያ ተሰበሰቡ፤ እሳቱ ሰውነታቸውን እንዳልጐዳው፥ ከራስ ጠጒራቸውም አንዲቱን እንኳ እንዳላቃጠለ፥ የመጐናጸፊያቸው መልክ እንዳልተለወጠና ሌላው ቀርቶ የእሳቱ ሽታ እንኳ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ በፊቴ መንገድን ያዘጋጅ ዘንድ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታም በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ በእርሱ የምትደሰቱበት የቃል ኪዳን መልእክተኛም በእርግጥ ይመጣል።”
ስለ ሙታን መነሣት የሆነ እንደ ሆነ ግን እግዚአብሔር ሙሴን ከቊጥቋጦው እሳት ውስጥ ምን እንደ ተናገረው ከሙሴ መጽሐፍ አላነበባችሁምን? ይኸውም ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤’ ያለው ነው።
ስለ ሙታን ትንሣኤ ግን፥ ሙሴ ስለ ቊጥቋጦው እሳት በተናገረው ታሪክ ውስጥ፥ ጌታን ‘የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ’ ብሎ ጠርቶታል።
‘እኔ የአባቶችህ አምላክ ነኝ፤ የአብርሃም አምላክ፤ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤’ ሙሴም በፍርሃት ተንቀጠቀጠ፤ ለመመልከትም አልደፈረም።
“የእስራኤል ሕዝብ ሙሴን ‘በእኛ ላይ ገዢና ፈራጅ እንድትሆን ያደረገህ ማን ነው?’ በማለት ተቃውመውት ነበር፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይህንኑ ሙሴን በቊጥቋጦው ውስጥ በተገለጠለት መልአክ አማካይነት ገዢና ነጻ አውጪ አድርጎ ወደ እነርሱ ላከው።
አጋር በዐረብ አገር ለሚገኘው ለሲና ተራራ ምሳሌ ነበረች፤ ስለዚህ ከአሁኒቱ ኢየሩሳሌም ጋር ትመሳሰላለች፤ እርስዋ ከነልጆችዋ በባርነት የምትገኝ ናት።
ምድራቸው ምርጥ በሆነ ነገር ሁሉ የተመላ ይሁን፤ በሚቃጠለው ቊጥቋጦ ውስጥ ከተገለጠው አምላክ ጸጋ ይብዛለት። ከወንድሞቹ መካከል ግንባር ቀደም ለሆነው ልዑል ለዮሴፍ ይደረግለት።
እናንተ ግን እሳት እንደሚነድበት የብረት ምድጃ ከሆነችው ከግብጽ መንጥቆ እግዚአብሔር ያወጣችሁ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ለራሱ የተለያችሁ ወገኖቹ እንድትሆኑ ነው።