ይህንንም ራእይ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ በዐይኖቹ መካከል ትልቅ ቀንድ ያለው አንድ አውራ ፍየል ምድርን አቋርጦ እግሮቹ መሬት ሳይነኩ ከምዕራብ በኩል እየበረረ መጣ።
ሐዋርያት ሥራ 4:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንግዲህ በእነዚህ ሰዎች ላይ ምን እናድርግ? ይህ ታላቅ ተአምር በእነርሱ እጅ መደረጉ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ታውቆአል፤ ስለዚህ ልንክደው አንችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም ተባባሉ፤ “እንግዲህ እነዚህን ሰዎች ምን እናድርጋቸው? በኢየሩሳሌም የሚኖር ሁሉ በእነርሱ እጅ የተደረገውን ድንቅ ታምር ዐውቋል፣ ስለዚህ ይህን ማስተባበል አንችልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በእነዚህ ሰዎች ምን እንሥራ? የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደ ተደረገበኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፤ እንሸሽገው ዘንድ አንችልም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አሉ፥ “እነዚህን ሰዎች ምን እናድርጋቸው? እነሆ፥ በእነርሱ የሚደረገው ተአምር በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ ግልጥም ሆነ፤ ልንሰውረውም አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደ ተደረገ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፥ እንሸሽገው ዘንድ አንችልም፤ |
ይህንንም ራእይ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ በዐይኖቹ መካከል ትልቅ ቀንድ ያለው አንድ አውራ ፍየል ምድርን አቋርጦ እግሮቹ መሬት ሳይነኩ ከምዕራብ በኩል እየበረረ መጣ።
አውራው ፍየል እጅግ እየበረታ ሄደ፤ ከኀያልነቱም የተነሣ ታላቅ የነበረው ቀንዱ ተሰበረ፤ በቦታውም አራት ታላላቅ ቀንዶች ተተኩ፤ እያንዳንዱም ቀንድ ወደተለያየ አራት አቅጣጫ ያመለክት ነበር፤