Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 8:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ይህንንም ራእይ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ በዐይኖቹ መካከል ትልቅ ቀንድ ያለው አንድ አውራ ፍየል ምድርን አቋርጦ እግሮቹ መሬት ሳይነኩ ከምዕራብ በኩል እየበረረ መጣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህም ነገር እያሰብሁ ሳለሁ፣ በዐይኖቹ መካከል ትልቅ ቀንድ ያለው አውራ ፍየል፣ መሬት ሳይነካ ምድርን ሁሉ እያቋረጠ በድንገት ከምዕራብ መጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እኔም ስመለከት፥ እነሆ፥ ከምዕራብ ወገን አንድ አውራ ፍየል በምድር ሁሉ ፊት ላይ ወጣ፥ ምድርንም አልነካም፥ ለፍየሉም በዓይኖቹ መካከል አንድ ታላቅ ቀንድ ነበረው።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 8:5
7 Referencias Cruzadas  

አውራው ፍየል የሚያመለክተው የግሪክን ንጉሥ ነው፤ በዐይኖቹ መካከል ያለው ትልቅ ቀንድ ደግሞ የመጀመሪያውን የግሪክ ንጉሥ ያመለክታል።


“ከዚያን በኋላ ጦረኛ የሆነ አንድ ብርቱ ንጉሥ ይነሣል፤ የመንግሥቱ ግዛት ታላቅ ይሆናል፤ የፈለገውንም ሁሉ ያደርጋል።


አውራው ፍየል እጅግ እየበረታ ሄደ፤ ከኀያልነቱም የተነሣ ታላቅ የነበረው ቀንዱ ተሰበረ፤ በቦታውም አራት ታላላቅ ቀንዶች ተተኩ፤ እያንዳንዱም ቀንድ ወደተለያየ አራት አቅጣጫ ያመለክት ነበር፤


“ይህንን በመመልከት ላይ ሳለሁ እነሆ፥ ሌላ ነብር የሚመስል አውሬ ወጣ፤ እርሱም የወፍ ክንፎች የሚመስሉ አራት ክንፎች በጀርባው ላይ ነበሩት፤ አራት ራሶችም ነበሩት፤ የገዢነት ሥልጣንም ተሰጠው።


ከአንተ በኋላ በገናናነቱ የአንተን መንግሥት የሚያኽል አነስተኛ መንግሥት ይነሣል፤ ከእርሱም ቀጥሎ ዓለምን ሁሉ የሚገዛ በነሐስ የሚመሰል መንግሥት በሦስተኛ ደረጃ ይነሣል።


የምስሉ ራስ ከንጹሕ ወርቅ፥ ደረቱና እጆቹ ከብር፥ ሆዱና ጭኖቹ ከነሐስ፤


እርሱም በወንዙ አጠገብ ቆሞ ወዳየሁት ሁለት ቀንዶች ወዳሉት በግ በታላቅ ቊጣ ተንደርድሮ መጣበት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios