ሐዋርያት ሥራ 24:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሁለት ዓመት በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ቦታ ተተካ፤ ፊልክስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ፈልጎ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላም፣ ፊልክስ በጶርቅዮስ ፊስጦስ ተተካ፤ ፊልክስም አይሁድን ለማስደሰት ሲል፣ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት ዓመትም ከሞላ በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደታሰረ ተወው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ዓመትም ካለፈ በኋላ፥ ፊልክስ ተሻረና ጶርቅዮስ ፊስጦስ የሚባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእርሱ ቦታ መጣ፤ ፊልክስም በግልጥ ለአይሁድ ሊያዳላ ወደደ፤ ስለዚህም ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ዓመትም ከሞላ በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው። |
ይህ ነገር አይሁድን ደስ እንዳሰኛቸው ባየ ጊዜ ጴጥሮስንም ደግሞ አስያዘው፤ ይህም የሆነው አይሁድ የቂጣ በዓልን በሚያከብሩባቸው ቀኖች ነበር።
እዚያም ብዙ ቀን በመቀመጣቸው ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ እንዲህ ሲል ለንጉሥ አግሪጳ ገለጠ፤ “ፊልክስ አስሮ የተወው እዚህ አንድ ሰው አለ፤
ፊስጦስ ግን አይሁድን ደስ ለማሰኘት ፈልጎ ጳውሎስን “ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ ስለዚህ ጉዳይ እዚያ በእኔ ፊት ልትፋረድ ትፈልጋለህን?” አለው።
ታዲያ፥ እኔ የምፈልገው ሰው እንዲያመሰግነኝ ነውን? ወይስ እግዚአብሔር እንዲያመሰግነኝ? ወይስ ሰውን ደስ ለማሰኘት የምፈልግ መስሎአችሁ ይሆን? ሰዎችን ለማስደሰት የምፈልግ ብሆን ኖሮ የክርስቶስ አገልጋይ ባልሆንኩም ነበር።