ሐዋርያት ሥራ 23:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመቶ አለቃውም ልጁን ወደ አዛዡ ይዞ ገባና “እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶኝ ይህ ልጅ ለአንተ የሚነግርህ ነገር ስላለው ወደ አንተ እንዳቀርበው ለመነኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ወደ ጦር አዛዡ ወሰደው። የመቶ አለቃውም፣ “እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶኝ፣ ይህ ጕልማሳ የሚነግርህ ነገር ስላለው ወደ አንተ እንዳቀርበው ለመነኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ይዞት ወደ ሻለቃው ወሰደውና “ይህ ብላቴና የሚነግርህ ነገር ስላለው እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶ ወደ አንተ እንድወስደው ለመነኝ፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመቶ አለቃውም ልጁን ይዞ ወደ የሻለቃው ወሰደውና፥ “የሚነግርህ ስለ አለው እስረኛው ጳውሎስ ይህን ልጅ ወደ አንተ እንዳደርሰው ለመነኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ይዞት ወደ ሻለቃው ወሰደውና፦ ይህ ብላቴና የሚነግርህ ነገር ስላለው እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶ ወደ አንተ እንድወስደው ለመነኝ አለው። |
ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ ጳውሎስንና ሌሎችንም እስረኞች በአውግስጦስ ክፍለ ጦር ውስጥ ለነበረው ዩልዮስ ለሚባለው መቶ አለቃ አስረከቡአቸው።
ከሦስት ቀን በኋላ ጳውሎስ በሮም የሚኖሩትን የአይሁድን ታላላቅ ሰዎች አስጠራ፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ በእስራኤል ሕዝብ ላይና በአባቶች ሥርዓት ላይ ያደረግኹት ምንም በደል የለም፤ ይሁን እንጂ በኢየሩሳሌም ታስሬ ለሮማውያን ተላልፌ ተሰጠሁ።