በዚህ ዐይነት የጌታ ቃል በጣም እየተስፋፋና ድል እያደረገ ይሄድ ነበር።
በዚህ ሁኔታ የጌታ ቃል በኀይል እያደገና እያሸነፈ ሄደ።
እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።
እንዲህም እያለ የእግዚአብሔር ቃል በኀይል ያድግና ይበረታ ነበር።
ከእኔ አንደበት የሚወጣውም ቃል እንደዚሁ ነው። እርሱ የላክሁትን ጉዳይ ሳያከናውንና ተልእኮውን ሳይፈጽም ወደ እኔ አይመለስም።
የእግዚአብሔር ቃል ግን ዘወትር እያደገና እየተስፋፋ ይሄድ ነበር።
አገረ ገዢውም የሆነውን ነገር ባየ ጊዜ አመነ፤ ስለ ጌታ በሰማውም ትምህርት ተደነቀ።
ጳውሎስ ይህን ያደረገው ለሁለት ዓመት ያኽል ነው፤ በዚያም ጊዜ በእስያ የሚኖሩ አይሁድና አሕዛብ ሁሉ የጌታን ቃል ለመስማት ቻሉ።
በዚህ ሁኔታ የእግዚአብሔር ቃል እየተስፋፋ ስለ ሄደ፥ በኢየሩሳሌም የአማኞች ቊጥር በጣም እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም እጅግ ብዙዎቹ አመኑ።
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ዘንድ እንደሆነው ሁሉ የጌታ ቃል በፍጥነት እንዲስፋፋና እንዲከበር ለእኛ ጸልዩልን፤