የወይን ጠጁን በብርሌ ሳይሆን በገምቦ ትጠጣላችሁ፤ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ሽቶ ትቀባላችሁ፤ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ስለ ደረሰው ጥፋት ግን ፈጽሞ አታዝኑም፤ ይህን ሁሉ ስለምታደርጉ ወዮላችሁ!
ሐዋርያት ሥራ 18:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ሁሉም የምኲራብ አለቃውን ሶስቴንስን ይዘው በሸንጎው ፊት ደበደቡት፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ጋልዮስ ደንታ አልነበረውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ሁሉም የምኵራቡን አለቃ፣ ሶስቴንስን ይዘው በፍርድ ቤቱ ፊት ደበደቡት፤ ጋልዮስ ግን ነገሩ ደንታም አልሰጠውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግሪክ ሰዎችም ሁሉ የምኵራብ አለቃ ሶስቴንስን ይዘው በወንበሩ ፊት መቱት፤ በእነዚህም ነገሮች ጋልዮስ ግድ የለውም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አረማውያንም ሁሉ የምኵራቡን አለቃ ሶስቴንስን ይዘው በሸንጎ ፊት ደበደቡት፤ የእርሱም ነገር ጋልዮስን ምንም አላሳዘነውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የግሪክ ሰዎችም ሁሉ የምኩራብ አለቃ ሶስቴንስን ይዘው በወንበሩ ፊት መቱት፤ በእነዚህም ነገሮች ጋልዮስ ግድ የለውም ነበር። |
የወይን ጠጁን በብርሌ ሳይሆን በገምቦ ትጠጣላችሁ፤ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ሽቶ ትቀባላችሁ፤ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ስለ ደረሰው ጥፋት ግን ፈጽሞ አታዝኑም፤ ይህን ሁሉ ስለምታደርጉ ወዮላችሁ!
ከዚህም በላይ ጲላጦስ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ በንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።