ሐዋርያት ሥራ 13:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! የኃጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ የኀጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ የኀጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ወንድሞቻችን፥ በእርሱ ኀጢአታችሁ እንደሚሰረይላችሁ ተስፋ የሰጣችሁን ዕወቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን። |
ከእንግዲህ ወዲህ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ ባልንጀራውንም ሆነ ወንድሙን የሚያስተምር ማንም አይኖርም፤ ከትልቁ ጀምሮ እስከ ትንሹ ሁሉም ያውቁኛል፤ በደላቸውን ይቅር እልላቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውንም አላስታውስባቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እኔ የማደርገውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ብዬ የማላደርግ መሆኔ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ ስለዚህ እስራኤል ሆይ! በአካሄዳችሁ ኀፍረትና ውርደት ይሰማችሁ።” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።
“ሰባት ጊዜ ሰባ ሳምንት የተባለው እግዚአብሔር ሕዝብህንና የተቀደሰ ከተማህን ከኃጢአትና ከክፋት ነጻ ለማውጣት ውሳኔ ያደረገበት ጊዜ ነው፤ በዚያን ጊዜ በደል ይሰረያል፤ ዘለዓለማዊ ፍትሕ ይሰፍናል፤ ራእይና ትንቢት ይፈጸማል፤ ቤተ መቅደሱም ይታደሳል።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ከዐሥራ አንዱ ጋር ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “እናንተ የይሁዳ ምድር ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ፥ ይህን የሆነውን ነገር ለማወቅ ንግግሬን አዳምጡ፤
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤
ይህ ሰው ድኖ በፊታችሁ የቆመው እናንተ በሰቀላችሁትና እግዚአብሔር ግን ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሆነ ለእናንተ ለሁላችሁና ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።
ይልቅስ እርስ በርሳችሁ ደጎችና አዛኞች ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።
አሁን ግን ኢየሱስ አማካይ አስማሚ የሆነበት ቃል ኪዳን ከአሮጌው ቃል ኪዳን የበለጠና በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሠረተ እንደ መሆኑ ለእርሱ የተሰጠው አገልግሎት የበለጠ ነው።