ሐዋርያት ሥራ 12:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ አስገደለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ አስገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። |
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
ኢየሱስም “በእርግጥ እኔ የምጠጣውን የመከራ ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን ሰዎችን በቀኜና በግራዬ እንዲቀመጡ የማደርገው እኔ አይደለሁም፤ ይህ ቦታ የሚሰጠው አባቴ ላዘጋጀላቸው ሰዎች ነው።”
ኢየሱስ ግን “የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ የምጠጣውን (የመከራ) ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን? እኔስ የምጠመቀውን ጥምቀት መጠመቅ ትችላላችሁን?” አላቸው።
እነርሱም “አዎ፥ እንችላለን፤” አሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእርግጥ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤