2 ተሰሎንቄ 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ሊሠራ የማይፈልግ አይብላ” የሚል ደንብ ሰጥተናችሁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ ጋራ በነበርንበት ጊዜ፣ “ሊሠራ የማይወድድ አይብላ” ብለን ይህን ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ማንም ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን “ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን፦ ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ ነበርና። |
ኢየሱስም፥ “ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ለሙሴ በተሰጠው ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም አለበት ብዬ የነገርኳችሁ ቃል ይህ ነው” አላቸው።
ይህንን ለእናንተ መናገሬ ግን ጊዜው ሲደርስ ምን እንዳልኳችሁ እንድታስታውሱ ነው።” “ይህን ሁሉ ከአሁን በፊት ያልነገርኳችሁ ከእናንተ ጋር ስለ ነበርኩ ነው፤
ወደ እርሱ በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወደ እስያ ከገባሁበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርኩ እናንተ ታውቃላችሁ፤